AmharaNationalmovement

ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የምክክር ሂደቱ ላይ የተነሱበትን ቅሬታዎች ውድቅ አደረገ

ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የምክክር ሂደቱ ላይ የተነሱበትን ቅሬታዎች ውድቅ አደረገ

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የምክክር ሂደቱን «ተዓማኒነት»፣ «አካታችነት»፣ «ገለልተኝነት» እና «ፍትሐዊነት» ጥያቄ ውስጥ የሚከቱ ተደጋጋሚና የተደራጁ ጥፋቶች ተፈጽመዋል በሚል ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምላሽ ሰጥቷል። ኮሚሽኑ አብን ነሀሴ 08 ቀን 2019 ዓ.ም ላወጣው መግለጫ በሰጠው ምላሽ፣ ፓርቲው ሂደቱ «አካታች» እና «አሳታፊ» አይደለም በሚል ያቀረበውን መግለጫ መመርመሩንና ማጣራቱን ገልጾ፣ የፓርቲውን ድምዳሜ እንደማይቀበለው ይፋ አድርጓል። ፓርቲው ወደ ምክክሩ የገባው ችግሮች በኃይል ሳይሆን በውይይት፣ በጫና ሳይሆን በመደማመጥ፣ በአንድ ወገን የበላይነት ሳይሆን በጋራ መግባባት፣ እንዲሁም ሁሉም አሸናፊ በሚሆንበት ሰጥቶ የመቀበል መርህ እንደነበር በመግለጫው አስታውሷል። ሆኖም በሂደቱ ውስጥ ከተራ የአሰራር ግድፈት የተለየ ሁኔታ መመልከቱን የዘረዘረው አብን፣ ሂደቱን ጥያቄ ውስጥ የሚከቱ ተዓማኒነትን፣ አካታችነትንና ፍትሐዊነትን…
Read More