30
Oct
በኦሮሚያ ክልል በምሥራቅ አርሲ ዞን አስተዳደር በጉና፣ በመርቲ፤ በሸርካ እና በሆሎንቆ ዋቢ ወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች ላይ ማንነታቸው ባልታወቀ ታጣቂዎች የተፈጸሙትን አሰቃቂ ግድያዎች የቤተክርሲቲያኒቷ ቋሚ ሲኖዶስ አውግዟል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ሕይወታቸውን ያጡ ወገኖችን አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል፡፡ በመግለጫውም ጥቅምት 14 ለ15 ቀን 2018 ዓ.ም በጉናና መርቲ ወረዳዎች 17 ክርስቲያኖች፣ ጥቅምት 17 ለ18 ቀን 2018 ዓ.ም. በሸርካ ወረዳ 3 ክርስቲያኖች እንዲሁም ጥቅምት 18 ለ19 ቀን 2018 ዓ.ም. በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ 5 ክርስቲያኖች በድምሩ በጥቅምት ወር 2018 ዓ.ም. ብቻ 25 ኦርቶዶክሳውያን በድንገት ማንነታቸው ባልታወቀ ታጣቂዎች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን አስታውቋል፡፡ ግድያውም…