Ethiopiaexport

አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የ10 በመቶ ቀረጥ ጣለች

አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የ10 በመቶ ቀረጥ ጣለች

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአለም አቀፍ ንግድ ላይ አዲስ ታሪፍ እንዲጣል ያዘዙ ሲሆን ኢትዮጵያም ወደ አሜሪካ በምትልካቸው ምርቶች ላይ የ10 በመቶ ቀረጥ ተጥሎባታል። ፕሬዚዳንቱ በነጩ ቤተ መንግሥት በሰጡት መግለጫ አሜሪካ ከሌሎች ሀገራት ጋር በምታደርገው የንግድ ልውውጥ ላይ አዲስ የታሪፍ መጠኖችን መጣላቸውን አስታውቀዋል። እንደ ፕሬዝዳንቱ ገለጻ እርምጃው አሜሪካን ቀዳሚ ለማድረግ እና የንግድ ጉድለትን ለመቀነስ ያለመ ነው። በአብዛኛዎቹ ሀገራት ላይ የተጣለው ታሪፍ ከ10% እስከ 49% የሚደርስ ሲሆን፣ ኢትዮጵያም 10% ታሪፍ ተጥሎባታል። ኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ ከተሞች አበባ፣ ቡና፣ የቆዳ እና አልባሳት ምርቶችን በመላክ ላይ ስትሆን ተጨማሪ 10 በመቶ ቀረጥ ለመክፈል ትገደዳለች። አሜሪካ የንግድ ጉድለቷን ለመቀነስ እና የአሜሪካን ኢኮኖሚ ለመጠበቅ ይህን እርምጃ እንደወሰደች የገለፁት…
Read More
ኢትዮጵያ ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ አገኘች

ኢትዮጵያ ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ አገኘች

ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ወደ ውጭ ከተላኩ ምርቶች አንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ዶላር መገኘቱ ተገልጿል፡፡ በኢትዮጵያ ከሚገኙ የኢንዱስትሪ ፓርኮች በአራት ዓመታት ውስጥ ወደ ውጪ ሀገራት ከተላኩ ምርቶች አንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ዶላር መገኘቱን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ። በአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ በዓመት 17 ሚሊዮን ዶላር ገቢ የሚያስገኙ የተለያዩ የፕላስቲክ ቱቦዎችን የሚያመርት ፋብሪካ ተመርቆ ሥራ ጀምሯል። የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አክሊሉ ታደሠ፤ ኮርፖሬሽኑ ከሚያስተዳድራቸው 13 የኢንዱስትሪ ፓርኮች የተለያዩ ምርቶች ለውጭ ገበያ እየቀረቡ መሆኑን ተናግረዋል። ኢንዱስትሪ ፓርኮቹ ለተለያዩ ሀገራት ገበያ ከሚያቀርቧቸው ምርቶች በአራት ዓመታት ውስጥ አንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን ሀላፊው ተናግረዋል፡፡ ከውጭ ሀገራት ይገቡ የመበሩ ምርቶችን በሀገር…
Read More
የኢትዮጵያ የወጪ ንግድ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ጉድለት አሳየ

የኢትዮጵያ የወጪ ንግድ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ጉድለት አሳየ

የኢትዮጵያ የዘጠኝ ወራት የወጪ ንግድ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ጉድለት አሳየ። የንግድ እና ቀጠናዊ ውህደት ሚንስቴር እንደገለጸው ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከወጪ ንግድ 3 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ ነበር። ይሁንና የተገኘው ገቢ ግን በአንድ ቢሊዮን ዶላር ቀንሶ 2 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ተገኝቷል ተብሏል። ለገቢው መቀነስ የጸጥታ ችግሮች፣ ህገወጥ ንግድ፣ የዓለም ንግድ መቀዛቀዝ እና የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት በምክንያትነት ተጠቅሰዋል። ከተገኘው ገቢ ውስጥም ግብርና የ77 በመቶ ድርሻ ሲያዝ ቀሪው ማዕድን፣ ኢንዱስትሪ እና ኤሌክትሪክ ሽያጭ እንደሆኑ ሚንስቴሩ ገልጿል ባለፉት ሁለት ዓመታት በጦርነት ውስጥ የቆየችው ኢትዮጵያ የወጪ ንግዷ ተዳክሞ የቆየ ሲሆን በአሜሪካ የተጣለባት ማዕቀብ፣ ህገወጥ የማዕድን ገበያ መስፋፋት ለወጪ ንግዱ ዋነኛ ችግሮች…
Read More