Electioninethiopia

ኢትዮጵያ ለምርጫ ስርዓት ማጠናከሪያ የ30 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አገኘች

ኢትዮጵያ ለምርጫ ስርዓት ማጠናከሪያ የ30 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አገኘች

ኢትዮጵያ ዘላቂ ዲሞክራሲን ለማስፈን የሚያስችላትን የምርጫ ስርአት እንድታጠናክር ለማግዝ የሚውል የ30 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር የፋናንስ ድጋፍ ስምምነት ፈርማለች፡፡ ስምምነቱን የኢትዮጵያ ገንዘብ ሚኒስቴር፣ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና የተባበሩት መንግስታት የልማት ድርጅት መካካል ተፈርሟል፡፡ የበጀት ድጋፉ የምርጫ ቦርድ ተቋማዊ መዋቅርን ለማጠናከር ነፃ፣ ፍትሃዊ፣ አሳታፊ ፣ተአማኒና ደረጃውን የጠበቀ ምርጫና ህዝበ ውሳኔ እንዲያካሂድ ተቋሙን ማጠናከር፣ ከሲቪክ ተቋማት በጋራ በመሆን በምርጫ ሂደት የሴቶችና ወጣቶች ተሳትፎን ለማሳደግ ይውላል ተብሏል፡፡ እንዲሁም የበጀት ድጋፉ በኢትዮጵያ ነፃ ፍትሀዊ እና ተአማኒ ምርጫ እንዲያከሂድ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር እንደሚውልም የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ይህ የበጀት ድጋፍ ፕሮጀክት በሚቀጥሉት አራት አመታት ውስጥ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን የሀገሪቱን የምርጫ ስርአት በማጠናከር ዘላቂ ዴሞክራሲን ለማስፈን አስተዋጽኦ…
Read More
ወይዘሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ ከሀላፊነት ለቀቁ

ወይዘሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ ከሀላፊነት ለቀቁ

ወይዘሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ ከሀላፊነት ለቀቁ ከ2011 ዓ.ም ታህሳስ ወር ጀምሮ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ሆነው ስራ የጀመሩት ወይዘሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ በጠየና ምክንያት የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸውን ሰማያዊ ማረጋገጫ ባለው የፌስቡክ ገጻቸው ላይ ገልጸዋል፡፡ “ባለፉት  አራት አመት ከስድስት ወራት ሶስት ህዝበ ውሳኔዎችን እና አገራዊ ምርጫን በማካሄድ እና ፓለቲካ ፓርቲዎችን በማስተዳደር የተሰጡኝን ሃላፊነቶች ህጋዊነት ፍትሀዊነት እና ቅንነትን በተከተለ ሁኔታ ለማከናወን ስጥር ቆይቻለሁ” ብለዋል። “ሆኖም ጤናዬን በሚገባ ለመጠበቅ የረጅም ጊዜ እረፍት የሚያስፈልገኝ ሆኖ በመገኘቱ ከ ነሀሴ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቦርድ ሰብሳቢነቴ በገዛ ፍቃዴ  መልቀቄን ለተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ጽህፈት ቤት ሰኔ 5 ቀን 2015 ዓ.ም አሳውቄያለሁ” ሲሉም…
Read More