Benishangulgumuz

በአሶሳ ዞን የወርቅ ማዕድን ማውጫ ተደርምሶ የስድስት ሰዎች ህይወት አለፈ

በአሶሳ ዞን የወርቅ ማዕድን ማውጫ ተደርምሶ የስድስት ሰዎች ህይወት አለፈ

በአሶሳ ዞን በመንጌ ወረዳ ሸጎል ቀበሌ  አሚር ካምፕ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የወርቅ ማዕድን ማውጫ ተደርምሶ የስድስት ሰዎች ህይወት ማለፉን የወረዳው ፖሊስ ገልጿል። ነሃሴ 24 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 7 ሰዓት ገደማ በአካባቢው ለወርቅ ማዕድን ማውጣት ስራ ጉድጓድ በመቆፈር ላይ ከነበሩ ዘጠኝ ግለሰቦች መካከል የስድስት ሰዎች ህይወት ማለፉን የመንጌ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት አዛዥ ረዳት ኢንስፔክተር አሳድቅ አብዱልፈታህ ተናግረዋል። ቀሪ ሶስት ሰዎች ደግሞ በአደጋው ቀላል እና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል የተባለ ሲሆን ተጎጂዎች በመንጌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እና በአሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል ብለዋል። በወቅቱ ግለሰቦችን በህይወት ለመታደግ በሰውና በመኪና የታገዘ ጥረት ቢደረግም ቦታው አስቸጋሪ ከመሆኑ የተነሳ መታደግ እንዳልተቻለ ተናግረዋል።…
Read More
በመተከል ዞን በጉምዝ ታጣቂዎች የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 18 ደረሰ

በመተከል ዞን በጉምዝ ታጣቂዎች የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 18 ደረሰ

በመተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ በጉምዝ ታጣቂዎች የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 18 ደረሰ በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ በታጣቂዎች በተከፈተ ተኩስ 18 ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ ግድያው የተፈጸመው አርብ ሰኔ 30 ቀን 2015 ሲሆን፤ ከ8 በላይ ሰዎች ከፍተኛ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በሕክምና ላይ እንደሚገኙም ታውቋል፡፡ እንደነዋሪዎቹ ገለጻ ከሆነ የችግሩ መነሻ፤ አንድ የአካባቢው ነዋሪ ለሥራ በወጣበት ተገድሎ በመገኘቱ አስከሬኑን ለማምጣት በሄዱ የጸጥታ አካላት ላይ በአካባቢው የሚገኙ የጉምዝ ታጣቂዎች ተኩስ በመክፈታቸው ሲሆን፤ በዚህም በርካታ ሰዎች መገደላቸው ተነግሯል፡፡ ተኩሱን የከፈቱት ሽፍታ የነበሩ እና የሰላም ተመላሽ ተብለው ትጥቃቸውን ሙሉ ለሙሉ ለመንግሥት እንዲያስረክቡ ከተጠየቁ ታጣቂዎች መካከል ትጥቅ ያልፈቱ እና በጫካ የሚኖሩ ታጣቂዎች…
Read More