AI

ኢትዮጵያ የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ዩኒቨርሲቲ ልትገነባ መሆኑ ተገለጸ

ኢትዮጵያ የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ዩኒቨርሲቲ ልትገነባ መሆኑ ተገለጸ

ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ዩኒቨርሲቲ ልትገነባ መሆኑንና ለዚህም የሚረዱ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ውስጥ እንደሚጠናቀቁ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 75ኛ ዓመት የምሥረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ ''የምሁራን ሚና ለሀገር ብልፅግና'' በሚል መሪ ሃሳብ በተካሄደ ውይይት ላይ እንደተናገሩት፤ በቴክኖሎጂው ዘርፍ መሽቀዳደም የግድ ይላል ብለዋል። አሁን ላይ በዓለማችን አንድ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ዩኒቨርሲቲ ብቻ የሚገኝ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ የሚገነባው ደግሞ የዓለማችን ሁለተኛው ይሆናል ማለታቸውንም ጋዜጣ ፕላስ ዘግቧል። ዩኒቨርሲቲው በቁጥር ጥቂት ነገር ግን ከፍተኛ ብቃት ያላቸውን 1 ሺህ ተመራቂዎች ለማፍራት ያለመ መሆኑን ዐቢይ (ዶ/ር) አስረድተዋል። እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ፤ ለሁሉም…
Read More
ቴክኖ ሞባይል  በኤይ አይ የታገዙ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ምርቶቹን አስተዋወቀ

ቴክኖ ሞባይል  በኤይ አይ የታገዙ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ምርቶቹን አስተዋወቀ

ቴክኖ ሞባይል የቴክኖ ኤአይ አጋዥ መተግበሪያን እና አዳዲስ በኤይ አይ የታገዙ የቴክኖሎጂ ምርቶቹን አስተዋውቋል፡፡ ቴክኖ ሞባይል በቅርቡ ለዓለም ያስተዋወቀው የቴክኖ ኤአይ አጋዥ መተግበሪያን እና አዳዲስ በኤይ አይ የታገዙ የቴክኖሎጂ ምርቶቹን በአዲስ አበባ ይፋ አድርጓል፡፡ አዲሱ የቴክኖ ኤአይ (Tecno AI) አጋዥ ቴክ ቋንቋን ከመተርጎም አንስቶ ፎቶን በራሱ አቅም ኤዲት ማድረግ፣ የተለያዩ ድምጾችን ወደ ፅሁፍ መቀየር እና መሰል ተያያዥ ስራዎች በቀላሉ እና በፍጥነት ለመስራት የሚያስችል አጋዥ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ወይም የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂን ተካቶለታል ተብሏል፡፡ የቴክኖ ኢትዮጵያ ብራንድ ማናጀር አቶ አሊክ "ቴክኖ በኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ላይ ጉልህ ሚናን እየተጫወተ እንደሚገኝ" ጠቅሰዋል። አቶ አሊክ "ቴክኖ ኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ በላይ ለህብረተሰቡ ተደራሽ መሆኑን…
Read More