Africanclimatechangesummit

የኢትዮጵያ ሙቀት በየዓመቱ ከአንድ ድግሪ ሴልሺየስ በላይ እየጨመረ መሆኑ ተገለጸ

የኢትዮጵያ ሙቀት በየዓመቱ ከአንድ ድግሪ ሴልሺየስ በላይ እየጨመረ መሆኑ ተገለጸ

በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በኢትዮጵያ የሙቀት መጠን በየዓመቱ በአማካይ ከ1 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እየጨመረ ነው ተብሏል ኢትዮጵያ ለአለም ሀገራት የሙቀት መጨመር ያላት የበካይ ጋዝ ልቀት ድርሻ ግን 0.04 በመቶ ነው ተብሏል፡፡ ያደጉት ሀገራት ለአፍሪካ በየጉባኤው ቃል የሚገቡትን የአየር ንብረት ለውጥ መደገፊያ የፋይናንስ ድጋፍ እየሰጡ ስላልሆነ የአየር ንብረት ለውጥ መከላከል የሚሰራው ስራ የሚፈለገውን ያህል መሆን አልቻለም ተብሏል፡፡ ይህ የተነገረው በአየር ንብረት ለውጥ ላይ የሚመክረውና ኢትዮጵያ ከጳጉሜ 3 እስከ 5 ከምታሰናዳው ሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ አስቀድሞ በተሰናዳ ዝግጅት ላይ ነው፡፡ የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ዛሬ ያሰናዳውና ነገም የሚቀጥለው ጉባኤና ኢግዚብሽን ከዋናው ጉባኤ በፊት የሚደረግ ቅድመ ጉባኤ ስለመሆኑ ተናግሯል፡፡ በዝግጅቱ መክፈቻ…
Read More
የመጀመሪያው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ በናይሮቢ መካሄድ ጀመረ

የመጀመሪያው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ በናይሮቢ መካሄድ ጀመረ

ከድርቅ ጀምሮ እስከ በርሃማነት በተደቀነባት የአፍሪካ አህጉር የወደፊት እጣ ፋንታ ላይ የሚመክር የአየር ንብረት ጉባኤ በናይሮቢ መካሄድ ጀምሯል። በኬንያ አስተናጋጅነት የሚካሄደው ጉባኤ ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ቀናት ይካሄዳልብተብሏል። በጉባኤው ላይ ከ20 ቡላይ የአፍሪካ መሪዎች፣ የበርካታ ሀገራት ሚንስትሮች፣ ልዑኮችና የአየር ንብረት ተሟጋቾች ይሳተፋሉ። በአህጉሪቱ እንደ ኢትዮጵያ፣ ሶማሊያና ኬንያ ባሉ ሀገራት ከ40 ዓመታት ወዲህ የከፋ የተባለ ድርቅ ተከስቷል። በዚህም በአፍሪካ ቀንድ እና በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የምግብ ዋስትና ቀውስ የተከሰተ ሲሆን፤ 10 ሚሊዮን የሚሆኑ እንስሳት ሞተዋል። የአፍሪካ ልማት ባንክ እንደሚለው እየጨመረ ከመጣው የአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ በሚከሰቱ አደጋዎች ሀገራት በየዓመቱ ከሰባት እስከ 15 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ሀብታቸውን ያጣሉ። የአየር ንብረት ለውጥን መከላከል ካልተቻለ…
Read More