Abesano

ኢትዮጵያ 78 በመቶ የሬሚታንስ ገቢዋን እንደምታጣ ተገለጸ

ኢትዮጵያ 78 በመቶ የሬሚታንስ ገቢዋን እንደምታጣ ተገለጸ

ሀገሪቱ ከሬሚታንስ ገቢ 35 ቢሊዮን ዶላር ገቢ የማግኘት አቅም እንዳላት ተገልጿል ኢትዮጵያ ከውጭ ሀገራት በሕጋዊ መንገድ ከሚላክላት ገንዘብ (ሬሚታንስ) የምታገኘው ገቢ የሀገሪቱን አቅም 22 በመቶ ብቻ መሆኑ ተገልጿል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ በተለያዩ ሀገራት ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ዲያስፖራዎች ጋር በመወያየት ላይ ናቸው፡፡ ከዚህ በፊት በተባበሩት አረብ ኢምሬት እና ሳውዲ አረቢያ ከተሞች ከኢትዮጵያዊያን ዲያስፖራዎች ጋር የተወያዩት ፕሬዝዳንቱ አሁን ደግሞ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ከተማ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር ተወያይተዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ በዚህ ጊዜ እንዳሉት ኢትዮጵያ ከሬሚታንስ ገቢ እየተገኘች ያለው ገቢ 7.2 ቢሊየን ዶላር ብቻ ነዉ ብለዋል። አቶ አቤ ሳኖ እንዳስረዱት፣ አሁን ካለው የገንዘብ ፍሰት ቀሪው 78 በመቶ የሚሆነው ወደ ሀገር…
Read More
የኢትዮጵያ ትልቁ ባንክ ከቻይናው የቴክስታይል ኩባንያ ጋር ስምምነት ተፈራረመ

የኢትዮጵያ ትልቁ ባንክ ከቻይናው የቴክስታይል ኩባንያ ጋር ስምምነት ተፈራረመ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለሠራተኞቹ የደንብ ልብስ ከሚያቀርብ የቻይና ቴክስታይል ኩባንያ ጋር ተፈራርሟል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለሠራተኞቹ የደንብ ልብስ አቅርቦት ከቻይናው ጂያንግሱ ሰንሻይን ግሩፕ ጋር መፈራረሙን አስታውቋል። የንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቤ ሳኖ ጥራት ያለው የደንብ ልብስ ለሠራተኞች እንዲቀርብ የሚያስችል ውይይት ከጂያንግሱ ሰንሻይን ግሩፕ ተወካዮች ጋር መወያየታቸው ተመላክቷል፡፡ ለደንብ ልብስ አቅርቦቱ ባንኩ ከፍተኛ ወጪ በመመደብ ለአብዛኛው ሠራተኛ ወጪውን የሸፈነ ሲሆን፣ በመካከለኛና ከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ የባንኩ ሠራተኞች እንዲሁም የሥራ ኃላፊዎች ደግሞ የተወሰነ ወጪ ተጋርተው የሚቀርብ መሆኑን አቶ አቤ ገልፀዋል፡፡ የጂያንግሱ ሰንሻይን ግሩፕ በኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሚ/ር ጋዊ ቻንሁሀ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ደንብ ልብስ ተቋማቸው በኢትዮጵያ ቅርንጫፉ ከሚሰራቸው አቅርቦቶች ትልቁ…
Read More