መነሻ ገፅ

በኢትዮጵያ የኩላሊት እጥበት በሚያደርጉ ህሙማን ላይ 50 በመቶ የዋጋ ጭማሪ ተደረገ

በኢትዮጵያ የኩላሊት እጥበት በሚያደርጉ ህሙማን ላይ 50 በመቶ የዋጋ ጭማሪ ተደረገ

በኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣው የኩላሊት ህሙማን ቁጥር በርካቶችን ለችግር እየዳረገ እንደሚገኝ ተጠቁሟል ። የህሙማኑን አቅም እየፈተነ የሚገኘው አቅምን ያላገናዘበ የህክምና ወጪ የብዙዎችን ቤት እያንኳኳ ይገኛል ሲሉ የኩላሊት ህመምተኞች እጥበት በጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን አሰፋ ተናግረዋል። በአሁኑ ሰዓት በዳግማዊ ሚኒሊክ ፣ በዘውዲቱ እና በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታሎች 180 ህሙማን የነፃ ህክምና አገልግሎት እየተጠቀሙ ቢሆን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ህሙማን ዕድሉን ባለማግኘታቸው ችግር ላይ መውደቃቸውን አቶ ሰለሞን ጠቁመዋል። እነዚህ ህሙማን ከእዚህ ቀደም በግል የህክምና ተቋማት ለአንድ ጊዜ የኩላሊት እጥበት ይጠየቁ ከነበረው ክፍያ እስከ 50 ከመቶ ጭማሪ እንደተደረገባቸው ስራ አስኪያጁ ያነሱ ሲሆን በግል የህክምና ተቋማት ለአንድ ጊዜ እጥበት ይጠይቅ…
Read More
ኢትዮጵያ 500 ሺህ ሴቶችን ወደ ሳውዲ አረቢያ ልትልክ መሆኗን ገለጸች

ኢትዮጵያ 500 ሺህ ሴቶችን ወደ ሳውዲ አረቢያ ልትልክ መሆኗን ገለጸች

ኢትዮጵያ 500 ሺሕ ሴቶችን ወደ አረብ አገር ልትልክ ነው በኢትዮጵያ በተያዘው ዓመት 500 ሺሕ ሴቶችን ወደ አረብ አገራት በተለይም ወደ ሳውዲ አረቢያ ለሥራ ለመላክ በመንግሥት እቅድ መያዙ ተገለጸ፡፡ ይህን ተከትሎም በአማራ ክልል ኹሉም ዞኖች ሰሞኑን ወደ አረብ አገር ሄደው መስራት ለሚፈልጉ ወጣት ሴቶች ስልጠና ሊሰጥ መሆኑን ኢትዮ ነጋሪ ሰምታለች፡፡ ለአብነትም በምስራቅ ጎጃም ዞን ሦስት የስልጠና ማዕከላት የተዘጋጁ ሲሆን፣ በሞጣ፣ ደብረ ማርቆስ እና ደጀን ከተሞች ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ ለሆኑ ሴቶች የቤት አያያዝና ሌሎች አስፈላጊ የሥራ ስልጠናዎች እንደሚሰጡኢትዮ ነጋሪ ከዞኑ መረጃ አግኝታለች፡፡ ስልጠናው ለ20 ቀን በመንግሥት በነጻ የሚሰጥ መሆኑን የተገለጸ ሲሆን፤ ከስልጠናው በኋላ ፈቃደኛ የሆኑ ሴቶች ወደ ሳውዲ አረቢያ የሚያቀኑበት የዚህ…
Read More
የኢትዮጵያ አቪየሽን አካዳሚ ወደ ዩኒቨርሲቲ ደረጃ አደገ

የኢትዮጵያ አቪየሽን አካዳሚ ወደ ዩኒቨርሲቲ ደረጃ አደገ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪዬሽን አካዳሚ ወደ ዩኒቨርሲቲ ደረጃ በማደግ በኤሮስፔስ እና በተለያዩ የሆቴልና ቱሪዝም ዘርፎች በቅድመ ምረቃ እና ድሕረ ምረቃ ፕሮግራሞች ማስተማር ጀመረ። የአቪዬሽን አካዳሚ የአቪዬሽን ስልጠና ፕሮግራሞችን በአብራሪነት፣ የአውሮፕላን ቴክኒሻን፣ የካቢን ሰራተኛ፣ የአየር መንገድ ሽያጭ እና አገልግሎት እና ሌሎች ስልጠናዎችን ሲሰጥ ቆይቷል።  ወደ ዩኒቨርሲቲ ደረጃ ካደገ በኋላ በኤሮኖቲካል ኢንጂነሪንግ በቢኤስሲ ዲግሪ፣ በአውሮፕላን ጥገና ኢንጂነሪንግ በቢኤስሲ ዲግሪ፣ በአቪዬሽን ማኔጅመንት ቢኤስሲ ዲግሪ፣ በቱሪዝም እና ሆስፒታሊቲ ማኔጅመንት ቢኤ ዲግሪ እና ኤምቢኤ በአቪዬሽን ማኔጅመንት የመሳሰሉ የዲግሪ መርሃ ግብሮችን ጀምሯል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው እንደተናገሩት "ከቀጣይ እድገትና ኢንቨስትመንት በኋላ 65 ዓመት ያስቆጠረውን የኢትዮጵያ አቪዬሽን አካዳሚ ወደ ዩኒቨርሲቲ ደረጃ ማደጉ…
Read More