የምርጫ ቦርድ አዲስ አሰራር ተፅዕኖ እንደሚፈጥርባቸዉ ፓርቲዎች አስታወቁ

ስምንት የፖለቲካ ፓርቲዎች ምርጫ ቦርድ የዘረጋው አዲስ አሰራር በቀጣዩ ሀገር አቀፍ ምርጫ ላይ ተጽዕኖ እንደሚፈጥርባቸው አስታውቀዋል።

የቦርዱን አዲስ አሰራር የተቃወሙ ፓርቲዎች የህብር ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ  ፓርቲ (ህብር ኢትዮጵያ)፣ መላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)፣ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ( ባልደራስ) ትብብር ለኢትዮጵያ  አንድነት ፓርቲ፣ለኢትዮጵያ አማራ ግዮናዊ ንቅናቄ፣ የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ)፣የኢትዮጵያ ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ (ኢሶዴፓ)፣የዎላይታ ብሄራዊ ንቅናቄ (ዎብን) ፓርቲዎች ናቸው።

በዚህ በጋራ መግለጫቸው የሀገሪቱ አቅም ባልፈቀደበትና እንደ ሀገር  ግንዛቤ በሌለበት ቴክኖሎጂካል አሰራር  ለመስፈርትነት መጠቀም አግባብነት የለውም ብለዋል።

አካል ጉዳተኞች ከሁለት ሆስፒታሎች ማስረጃ እንዲያቀርቡ ግዴታ መቀመጡ፣ የአገሪቱን ገጠር አካባቢዎች ያላገናዘበና ሆስፒታሎች በሌሉበት ማስረጃ  መጠየቅ የአካል ጉዳተኞች ነባራዊ ሁኔታ የሚዳሰስና የሚታይ ሆኖ ሳለ ማስረጃ መጠየቁ በራሱ ትክክል አይደለም ሲሉ ተቃውመዋል፡፡

ኢትዮ ነጋሪ ስምንት የፖለቲካ ፓርቲዎች ያወጡንን መግለጫ መነሻ በማድረግ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድን አነጋግሯል።

በምርጫ ቦርዱ የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የተፎካካሪ ፓርቲዎችና የግል እጩዎች  መሪ  የሆኑት ቀነኒ  እንሰርሙ እንደገለጹት ቦርዱ  በቀጣይ በሚካሄደው 7ተኛው  ጠቅላላ ምርጫን ፤ ግልፅ ፣ ፍትሃዊና ታዓማኒነቱን ለማረጋገጥ በቴክኖሎጅ የታገዘ አሰራር ለመስራት ወስኖ የተለያዩ ቅድመ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

በዚህ ጉዳይ ላይ ለተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች አስቀድሞ የመረጃ እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ቦርዱ ሲሰጥ ቆይቷል ሲሉም አስታውቀዋል።

አሁንም ቦርዱ  የተሰጠው ሃላፊነት  የትኛውንም ተፎካካሪ ፓርቲ  በእኩልነት ማገልገል ስለሆነ ፓርቲዎች ተጨማሪ ድጋፍ ከፈለጉ ቦርዱን እንዲጠይቁም ዳይሬክተሯ ተናግረዋል ።

ሰባተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ የፊታችን ግንቦት ወር መጨረሻ ሳምንት ላይ የሚካሄድ  የእጩዎች ምዝገባ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

የተለያዩ ፓርቲዎች የሀገሪቱ የጸጥታ ሁኔታ ምርጫ ለማካሄድ ጊዜው በቂ እንዳልሆነ ቢገልጹም ምርጫ ቦርድ ግን ምርጫውን በሁሉም ክልሎች እንደሚያካሂድ እና እስካሁን ምርጫውን ማስተጓጎል የሚያስችል የጸጥታ ችግር እንዳልገጠመው አስታውቋል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *