በኢትዮጵያ የቤት ልማት ፕሮግራም ወይም ሪልኢስቴት ኢንዱስትሪ ውስጥ አንዱ የሆነው ጊፍት ሪል ስቴት በ15 በመቶ ቅናሽ ለፋሲካ በዓል የአፓርትመንትና የንግድ ሱቆችን ለሽያጭ ማቅረቡን አስታውቋል፡፡
የድርጅቱ ሽያጭ እና ማርኬቲንግ ዳይሬክተር አቶ ብርቁ ይርጋ በአዲስ አበባ ለገሀር ሳይት በተዘጋጀ ፕሮግራም ላይ እንዳሉት ጊፍት ሪል ኢስቴት ደንበኞች የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ በ2 በመቶ ቅድመ ክፍያ ብቻ ቤት መግዛት እንዲችሉ የሚያስችል ኤክስፖ ማዘጋጀቱን ገልፀዋል።
የሽያጭ ኤክስፖው ከመጋቢት 19 እስከ ሚያዚያ 19 ቀን 2018 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን 1 ሺህ 200 ቤቶች ለሽያጭ መቅረባቸውን ዳይሬክተሩ ተገልጿል።
በ2005. የተመሰረተው ጊፍት ሪል ስቴት ሦስት መንደሮችን ጨርሶ ለገዢዎች አስረክቧል የተባለ ሲሆን አራተኛውን የጊፍት ሜትሮፖሊታን መንደር በለገሃር ላይ 4 ሺህ ቤቶችን በመገንባት ላይ ይገኛል ተብሏል፡፡
ከነዚህ መካከል የ12 ሺህ ቤቶች ማስፋፊያ አካል የሆነ በሁለተኛና ሶስተኛ ዙሮች የሚገነቡ 8 ሺህ የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶች እንዲሁም በ6 ኪሎ ፣በቦሌ መድኃኒዓለም ፣ በፊጋ 1 በ22 ማዞሪያ ፤ በተክለሃይማኖት በሲ.ኤም.ሲ እና በሌሎች አካባቢዎች 4 ሺህ በአጠቃላይ ከ16 ሺህ በላይ ቤቶች መተዋወቃቸው ተገልጿል።
ከተመሰረተ ከ20 ዓመት በላይ የሆነው ጊፍት ሪል ኢስቴት በ2022 በታሪኩ ከፍተኛ የተባለውን ሽያጭ ገቢ እንዳከናወነ ተገልጿል።
በአጠቃላይ ጊፍት ሪል ኢስቴት ከስድስት ቢሊዮን ብር በላይ ሽያጭ እንዳካሄደ ሲገለጽ በኢትዮጵያ ሪል ኢስቴት ኢንዱስትሪ ውስጥ ባበረከተው አስተዋጽኦ ሽልማቶችን ማግኘቱ ተገልጿል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር በመንግስት እና የግል አጋርነት ፕሮግራም ከ100 ሺህ በላይ መኖሪያ ቤቶችን በመገንባት ላይ ሲሆን ጊፍት ሪል ኢስቴት የዚህ ፕሮግራም አካል እንደሆነ የድርጅቱ ማርኬቲንግ ዳይሬክተር አቶ ብርቁ ተናግረዋል።
ጊፍት ሪል ኢስቴት ከቤት ልማት ባለፈ በብረታ ብረት፣ ግንባታ፣ ማዕድን ማውጣት እና ሌሎች የኢንቨስትመንት መስኮች በመስራት ላይ እንደሆነ ተገልጿል።