ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለ3ኛ ጊዜ የህዳሴውን ግድብ ግንባታ ወጪ አሜሪካ መሸፈኗን ተናገሩ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ስልጣን የመጡበትን አንደኛ ዓመት አስመልክቶ ባደረጉት ንግግር የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ወጪ በሀገራቸው መሸፈኑን ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንቱ ስልጣን ላይ በቆዩባቸው ጊዜያት ስምንት ጦርነቶችን እንዳስቆሙ ገልጸው ኢትዮጵያ እና ግብጽም በህዳሴው ግድብ ምክንያት ሊያደርጉት የነበረውን ጦርነት ማስቆማቸውን ገልጸዋል።

“ኢትዮጵያ በናይል ወንዝ ላይ በገነባችው ትልቅ ግድብ ምክንያት ግብጾች ተጎድተዋል፣ ውሀቸው ቀንሶባቸዋል፣ ናይል ግብጽ ውስጥ ያለ ነበር እሚመስለኝ፣ ወንዙ ይህን ጉዳይ መፍታት እፈልጋለሁ” ብለዋል ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ።

“የግድቡን ግንባታ ወጪ ማን እንደሸፈነው ታውቃላችሁ? እኛው ነን” ያሉት ፕሬዝዳንት ትራምፕ በኢትዮጵያ እና ግብጽ መካከል ያለውን አለመግባባት የመፍታት እቅድ እንዳላቸውም ተናግረዋል።

ስለ ኢትዮጵያ ህዳሴው ግድብ በተደጋጋሚ ሲናገሩ የሚሰሙት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከዚህ በፊትም የግድቡን ወጪ ሀገራቸው መሸፈኗን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት በይፋ ፕሬዝዳንት ትራምፕ የህዳሴው ግድብ ግንባታ ወጪ በአሜሪካ መሸፈኑን አስመልክቶ የተደረገውን ንግግር በተደጋጋሚ ውድቅ አድርጓል።

ሙሉ ለሙሉ ግንባታው ተጠናቆ ሀይል ማመንጨት የጀመረው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴው ግድብ የግንባታው ወጪ በኢትዮጵያውያን እና በመንግስት ወጪ መሸፈኑ ተገልጿል።

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባሳለፍነው ሳምንት ለግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ በጻፉት ደብዳቤ ግብጽ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ከኢትዮጵያ ጋር የገባችበትን አለመግባባት የመፍታት ፍላጎት እንዳላት መግለጻቸው ይታወሳል።

የዚህ ደብዳቤ ግልባጭ ለኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ እና ለሱዳን ጦር አዛዥ ጀነራል አልቡርሀን እንዲደርሳቸውም ተደርጓል።

በተጨማሪም ፕሬዝዳንት ትራምፕ ደብዳቤ ለሳውዲ አረቢያ እና የተባበሩት አረብ ኢምሬት ገዢዎች በግልባጭ እንዲደርሳቸው አድርገዋል።

ግብጽ እና ሱዳን የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን ጥያቄ በደስታ መቀበላቸውን ሲገልጹ ኢትዮጵያ እስካሁን ስለጉዳዩ ያለችው ነገር የለም።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *