በስመኝሽ ገብረወልድ
ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከር የ 43.3 በመቶ ወይም 18.9 ቢሊዮን ብር እድገት አሳይቷል ብሏል።
ገቢውም የእቅዱን 90.7 መሆኑን ተናግሯል።
በዘንድሮ የበጀት ዓመት ስድስት ወር ውስጥ ምንም አይነት የሳይበር ጥቃት አልደረሰብኝም ነው ያለው።
በዚሁ የስራ አፈፃፀም የግዜ ማዕቀፍ 6 ሚሊዮን ገደማ ደንበኞች አፍርቻለሁ ያለው ኩባንያው በአጠቃላይ የደንበኞቼ ቁጥርም 80.5 ሚሊየን ደርሰዋል ተብሏል።
ኢትዮ ቴሌኮም በቴሌኮም አገልግሎት ብዛት ከአፍሪካ 1ኛ ከዓለም ደግሞ 17ኛ ደረጃ ላይ መቀመጡን ዓለም አቀፉ የቴሌኮም አገልግሎት ድርጅት ወይም ጂ.ኤስ.ኤም.ኤ (GSMA) ጥናት ተረጋግጧል ተብሏል።
የደንበኛን ቁጥር ለመጨመር ከተሰሩት ስራዎች መካከል በግማሽ አመቱ 202 አዳዲስ የሞባይል ጣቢያዎች ተጠናቀው ወደ እንደገቡም ተገልጿል።
በሞባይል ኔትዎርክ በተከናወኑ የፕሮጀክት ስራዎች ተጨማሪ 4.6 ሚሊዮን የሞባይል ኔትዎርክ አቅም በመገንባት 86.1 ሚሊዮን የነበረውን የሞባይል ኔትወርክ አቅም ወደ 90.7 ሚሊዮን ማድረስ እንደተቻለ ወይዘሮ ፍሬህይወት በመግለጫው ላይ ተናግረዋል፡፡
በዚህም 67 ተጨማሪ ከተሞች የ4ጂ አገልግሎት ያገኙ ሲሆን ተጨማሪ 10 ከተሞች የ5ጂ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን ችለዋል፡፡
በተጨማሪም ማህበረሰቡን የዲጂታል ኢኮኖሚው ተጠቃሚ የሚያደርጉ ወቅታዊነትን የተላበሱ 62 አዳዲስ እና 109 ማሻሻያ በአጠቃላይ 171 የሀገር ውስጥ እና የዓለም አቀፍ ምርትና አገልግሎቶች ለደንበኞች ቀርበዋል፡፡
በተጨማሪም ኢትዮዽያን ከሌላ ሀገር የሚያገናኝበት ጌት ወይ መሰረተ ልማትም ፈጣንና የተሻለ እንዲሆን ማስፋፍያ ተደርጎለታል የተባለ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ኢንተርኔት ወደ ኢትዮጵያ የሚገባው በ5 መስመር ነው እነሱም ሱዳን፣ ጂቡቲ በሁለት በኩል፣ በሶማሌላንድ እና ኬኒያ ናቸው ተብሏል።
በሌላ በኩል በስድስት ወራት ውስጥ 8 ከተሞች የ5ጂ አገልግሎት አግኝተዋል ተብሏል።
ከማስፋፍያ ጎን ለጎንም በግጭት ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው 231 የሞባይል ጣቢያዎች ዳግም ጥገና ተደርጎላቸዋል።
በተጨማሪም ተቋሙ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ 23.74 ቢሊየን ብር ታክስ ለመንግስት ገቢ ያደረገ ሲሆን 15 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዶላር ወይም 1 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር የውጭ ብድር መክፈሉንም አስታውቋል።