ዳሸን ባንክ ዘ ባንከር የተሰኘውን ሽልማት አሸነፈ

ዳሸን ባንክ በተለያዩ ዘርፎች ባስመዘገበው የላቀ አፈጻፀም የ“ዘባንከር” ሽልማት ተሸላሚ ሆነ

ባንኮችን በተለያዮ የምርጥ አፈጻጸም መለኪያዎች የሚመዝነው የእንግሊዙ ፋይናንሻል ታይምስ የሚያሳትመው ዘባንከር መጽሔት ዳሸን ባንክ የ2024 የኢትዮጵያ አሸናፊ ሆኗል፡፡ 

የዳሸን ባንክ ቺፍ የደንበኞች አገልግሎት መኮንን ወ/ሪት እየሩሳሌም ዋጋው እና የዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ የፋይናንስ ዘርፍ አማካሪ አቶ ሙሉጌታ አለባቸው በእንግሊዝ ሎንዶን ተገኝተው ሽልማቱን ተቀብለዋል፡፡ 

በሽልማት ስነ-ስርዓቱ ላይ እንደተገለፀው ዳሸን ባንክ በዘርፉ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በማስተዋወቅ፣ አዳዲስ አገልግሎቶችን በማቅረብ እና ከተለያዩ አለምአቀፍና አህጉራዊ ባለድርሻ አካላት ጋር የፈጠረው ውጤታማ ጥምረት ለሽልማት አብቅቶታል ተብሏል፡፡ 

አቶ ሙሉጌታ አለባቸው በስነ-ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ሽልማቱ ዳሸን ባንክ በዲጂታል ቴክኖሎጂ አማካኝነትና እና ከተለያዩ አለም አቀፍና አህጉራዊ ተቋማት ጋር ጥምረት በመፍጠር አካታች አገልግሎት ለማቅረብ ላደረገው ጥረት ዕውቅና የሰጠ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

ወ/ሪት እየሩሳሌም ዋጋው በበኩላቸው “ይህ ሽልማት በዳሸን ባንክ ላይ ትልቅ ዕምነትና መተማመን አሳድረው አብረውን ለሚሰሩ ደንበኞቻችንና ሁሉም ባለድርሻ አካላት አማካኝነት የተሰጠ ዕውቅና ነው” ብለዋል፡፡

ዳሸን ባንክ ዘባንከር ሽልማትን ለ14ተኛ ጊዜ አሸናፊ የሆነ ሲሆን በአሁኑ ወቅት 6ተኛውን ስትራቴጂክ ዕቅዱን በመተግበር ለደንበኞቹ ከመቼውም ጊዜ በተሻለ መልኩ ጥራት ያለውና ቀልጣፋ አገልግሎት ለማቅረብ ጥረት እያደረገ መሆኑን አስታውቋል፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *