የአፍሪካ ፋሽን ሳምንት በአዲስ አበባ ተከፈተ

ከ30 ሀገራት በላይ የተውጣጡ ከ250 በላይ የፋሽን፣ ጨርቃጨርቅ እና ቆዳ ኢንዱስትሪዎችዎቸን በአንድ ጣራ ስር የሚያሰባስበው የአፍሪካ ሶርሲንግና ፋሽን ሳምንት በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ፡፡

በአፍሪካ አህጉር ትልቁ የጨርቃጨርቅ እና ፋሽን ኢንዱስትሪ ኤግዚቢሽን የሆነው “10ኛው የአፍሪካ ሶርሲንግ እና ፋሽን ሳምንት(10th AFRICA SOURCING AND FASHION WEEK  ASFW ) በአዲስ አበባ  ስካይ ላይት ሆቴል ከዛሬ ጥቅምት 29 እስከ ህዳር 02 ቀን 2017 ዓ.ም ይካሄዳል።

የፋሽን ሳምንቱን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስት አቶ መላኩ አለበል፣ ክብርት ሌንሳ መኮንን፣ በኢትዮጵያ የጀርመን ኤምባሲ እና ሌሎች በርካታ አንግዶች ከፍተውታል፡፡

ዝግጅቱ አለም አቀፍ ብራንዶችን፣ የኢንዱስትሪ መሪዎችን እና ፈጣሪዎችን በአንድ ጣሪያ ስር በማሰብሰብ እስካሁን  ከተደረጉት ዝግጅቶች ሁሉ ትልቁ  ያደርገዋል ተብሏል፡፡

የአፍሪካ ሶርሲንግና ፋሽን ሳምንት ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ በጨርቃ ጨርቅ፣ በአልባሳት እና የቆዳ እሴት ሰንሰለቶች መካከል ትብብርን በማጎልበት እና ንግድን በማመቻቸት በአህጉሪቱ ትልቁ የፋሽን መድርክ ሆኖ ቆይቷል፡፡

ዛሬ በተከፈተው እና ለመጪዎቹ አራት ቀናት በሚቆየው የፋሽን ፣ጨርቃጨርቅ እና ቆዳ ኢንዱስትሪዎችን በአንድ ጣራ ስር ያሰባሰበው ዝግጅት ከ30 ሀገራት በላይ የተውጣጡ ከ250 በላይ የዘርፉ ተዋኒያኖች ኤግዚቢሽኖችን ያሳያሉ፡፡

ከ60 በላይ ሀገራት የሚመጡ ከ7,000 በላይ የንግድ ሰዎችም ይታደማሉ የተባለ ሲሆን ይህም ለጎብኚዎች አና ተሳታፊዎች በፋሽን ኢንደስትሪ ዘርፍ አለም የደረሰችበትን ደረጃ አንዲገነዘቡ፣ፈጠራዎች የት አንደደረሱ አጠቃላይ እይታ ይሰጣልም ተብሏል።

ተሳታፊዎች አና ጎብኚዎች ወቅታዊን የጨርቃ ጨርቅ፣ሌዘር እና ፋሽን ኢንዱስትሪ  በተመለከተ  በኮንፈረንሶች እና የፓናል ውይይቶች ላይ ለመሳተፍ እድል ያገኛሉ።

የዘርፉ ባለሞያዎች በአፍሪካ የፋሽን እይታ ላይ በዘለቄታው መሰራት ስላለባቸው ጉዳዮች ፣ የቴክኖሎጂ ፈጠራ እና የኢንቨስትመንት መላዎች ላይ ያተኮሩ  የፓናል ውይይቶች ያቀርባሉ፡፡

ይህ ልዩ ዝግጅት ለሸማቾች አዳዲስ ብራንዶችን ለማወቅ፣ ጥራት ያላቸውን ምርቶች ለማግኘት እና ትርጉም ያለው ወዳጅነት ለመመስረት በብርቱ ይረዳቸዋል፡፡

ይህ  10ኛውን የአፍሪካ ሶርሲንግ እና ፋሽን ሳምንት( 10th  AFRICA SOURCING AND FASHION WEEK)  ምክንያት አድርጎ የተዘጋጀ ልዩ 10ኛ-አመት ትዕይንት ነው፡፡

በዚህ የፋሽን ዘግጅት ዘመን የማይሽራቸው የቆዳ  ውጤቶች የሚጣበት ነው፡፡ከመላው አፍሪካ የተውጣጡ ምርጥ ዲዛይነሮች ስራን የሚታይበት ሲሆን ልዩ ፈጠራዎች የታዩባቸው የቆዳን ሁለገብነት አጉልተው የሚያሳዩ ምርቶች ይቀርባሉ፡፡

10ኛው የአፍሪካ ሶርሲንግ እና ፋሽን ሳምንት ዝግጅት የሚቀርበው ይህ የፋሽን ሳምንት 

የእጅ ጥበበኞችን እና የአሰራር ዘይቤያቸውን የምናከብርበት የማይረሳ ምሽት አንዲሆን ያደርገዋል።

የትሬድ ኤንድ ፌርስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ስካንደር ነጋሲ እንዳሉት “የአፍሪካ ሶርሲንግ እና ፋሽን ሳምንት 10ኛውን ዓመት ስናከብር የአፍሪካ ፋሽን እና ጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የወደፊት ዕጣ ፈንታ በመቅረጽ ለተጫወትነው ሚና ኩራት ይሰማናል። ይህ ወሳኝ ምዕራፍ ስኬቶቻችንን የምናይበት ብቻ ሳይሆን አጋሮቻችንን፣ ኤግዚቢሽን አቅራቢዎች እና ታዳሚዎቻችንን ለዓመታት ያደረጉትን የጋራ ጥረት ክብር የምንሰጥበት ነው። ብዙ አመለካከቶቸን፣ ደንቅ ፈጠራዎችን በማሰባሰብ እና ከምንም በለይ ዘላቂነት ላይ ትኩረት በማድረግ የዚህን አመት ዝግጅት ከእከዛሬዎቹ ትልቁ እና ተፅዕኖ ያለው ሁነት አናደርገዋል” ብለዋል፡፡

በመሴ ፍራንክፈርት የሥራ አመራር ቦርድ አባል የሆኑት ዴትሌፍ ብራውን በበኩላቸው ” የአፍሪካ ሶርሲንግ እና ፋሽን ሳምንት 10ኛ ዓመት  ክብረ በዓል ላይ በመድረሳችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡

ለዚህ ጉልህ  የጨርቃጨርቅ ዘርፍ እደገት ላይ አስተዋጾ ያደረጉ እና ተሳታፊዎች የሰሩትን  ስራዎች ወደ ኋላ መለስ ብለው በአዲስ አበባው መድረክ በኩራት ይመለከቱታል፡፡

እንደ መሴ ፍራንክፈርት፣ የASFW ቀጣይነት ያለው እድገት በማሳየቱ እና ተፅእኖ አሳዳሪ  ሆኖ በማየታችን አንዲሁም በአለም ላይ ከ50 በላይ የጨርቃጨርቅ ንግድ ትርኢቶችን በማየታችን በጣም ደስተኞች ነን ሲሉም ዴትሊፍ አክለዋል።

አሁን ያለንበት ምእራፍ የASFWን በአፍሪካ ፋሽን እና ሶርሲንግ  ኢንደስትሪ ውስጥ ያለውን አስፈላጊነት የሚያረጋግጥ ነው፡፡ይህም በፈጠራ ውስጥ ቀጣይነት ያለውት ደርጃዎች  ማስቀመጥ የሚያስችል ነው፡፡ ለሁሉም ተሳታፊዎች አበረታች እና ስኬታማ ኤግዚቢሽን አንዲሆን እየተመኘሁ ለመጪዎቹ ዓመታትም ትርጉም ያላቸው ትብብሮች አንደሚኖሩን እጠብቃለሁ ብለዋል፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *