ኢትዮጵያ ከቡና የምታገኘው ገቢ የ90 ሚሊዮን ዶላር ቅናሽ አሳየ

ኢትዮጵያ ወደ ውጭ ሀገራት ከተላከ ቡና 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አግኝታለች።

ኢትዮጵያ ለዓለም ገበያ የምታቀርበው የቡና ምርት መጠን ከዓመት ዓመት ማሽቆልቆሉን የኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች ማህበር ገልጿል፡፡

የማህበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅ ግዛት ወርቁ ኢትዮጵያ በ2014 ዓ. ም ለዓለም ገበያ ያቀረበችው የቡና መጠን 302 ሺሕ ቶን ነበር።

በዘንድሮው ማለትም በ2015 ዓመት ግን 240 ሺሕ ቶን ብቻ ቡና ለዓለም ገበያ ማቅረቧን የኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች ማህበር አስታውቋል።

ወደ ውጪ ሀገራት የተላከው ቡና ከባለፈው ዓመት ለዓለም ገበያ ከቀረበው የቡና ምርት ጋር ሲንጻጸር በ62 ሺሕ ቶን ቅናሽ አሳይቷል ተብላል።

ሥራ አስኪያጁ አክለውም፤ ኢትዮጵያ በዘንድሮው ዓመት ለዓለም ገበያ ካቀረበችው ቡና 1 ነጥብ 33 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አግኝታለች ብለዋል።

የተገኘው ገቢ ከባለፈው ዓመት ገቢ ጋር ሲነጻጸር በ90 ሚሊዮን ዶላር ቅናሽ አሳይቷል።

ቡናን ለዓለም ገበያ በማቅረብ ግንባር ቀደም የሆነችው ብራዚል ባለፈው ዓመት በተከሰተ ውርጭ እና ድርቅ ምክንያት የቡና አቅርቦቷ ቀንሶ ነበር።

ይህን ተከትሎም ኢትዮጵያ ለዓለም ገበያ የምታቀርበው የቡና መጠን ከፍ ብሎ እንደነበር ነው ሀላፊው ተናግረዋል ።

ኢትዮጵያ አሁን ላይ ለዓለም ገበያ የምታቀርበው በጥራት መለኪያ ደረጃ አምስት የተሰኘ ቡና በኪሎግራም በ3 ነጥብ 46 ዶላር ወይም 190 ብር በመሸጥ ላይ ስትሆን ትርፍ አያስገኝም ተብሏል።

ይሁንና አንድ ኪሎ ቡና በሀገር ውስጥ 400 ብር እየተሸጠ ሲሆን ቡና ላኪዎች ቡናቸውን ወደ ውጭ ሀገራት ከሚልኩት ይልቅ በሀገር ውስጥ ቢሸጡት አትራፊ ያደርጋቸዋል ።

በዚህ ምክንያት ቡና ወደ ውጭ ሀገራት የሚልኩ ላኪዎች ቁጥር እንዲቀንስ ከማድረጉ በላይ ኢትዮጵያ ከወጪ ንግድ የምታገኘውን የውጭ ምንዛሬ እንዲቀንስ እያሰረገ መሆኑን ሀላፊው ተናግረዋል ።

ከዚህ በተጨማሪም የሀገሪቱ ጸጥታ አስተማማኝ አለመሆን በቡና ላኪዎች ላይ ችግር እየፈጠረ ነው የተባለ ሲሆን መንግስት የደህንነት ስራውን እንዲሰራም ሀላፊው ጠይቀዋል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *