እስራኤል ሁለት ሺህ ቤተ እስራኤላዊያንን ከኢትዮጵያ ልትወስድ መሆኗን ገለጸች

የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያኹ ለመንግስታቸዉ ከኢትዮጵያዉያን ቤተ እስራኤላውያን ማህበረሰብ ጋር ያላቸዉን ግንኙነት ማጠናከር ባለባቸዉ ጉዳዮች ላይ ያቀረቡት እቅድ ጸድቋል።

በዚህ እቅድ መሰረትም 2 ሺህ ቤተእስራኤላውያንን ወደ ቴልአቪቭ ለመዉሰድ ማቀዳቸዉን ጀረሰላም ፖስት ዘግቧል።

እ.ኤ.አ በ 2015 የእስራኤል መንግስት 9 ሺህ የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን እስራኤል መግባት የሚፈልጉ ቤተ እስራኤላውያንን ጥያቄ ከተቀበለ በኋላ ባገጠመዉ የበጀት እጥረት ማጓጓዝ ሳይችል መቅረቱ ተዘግቧል።

በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀረበ የተባለዉ እቅድ ኢትዮጵያዊ ቤተ እስራኤላዊያንን ለማጓጓዝ 66 ሚሊዮን ዶላር በጀት ተይዞለታልም ተብሏል።

የሀገሪቱ መንግስት በእስራል ከሚገኙ ከ 160 ሺህ በላይ ቤተ እስራኤላውያን ዜጎች ጋር ያለዉን ግንኙነት  በማጠናከር በተለይም ወደ ሀገሪቱ የጦር ሀይል ለማካተት እቅድ እንዳለዉ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል።

በተጨማሪም በእስራኤላውያን እና በቤተ እስራኤላውያን መካከል እንዲሁም በመንግስት በኩል ያለዉን እምነት ማጠናከር ትኩረት ከተሰጣቸው ጉዳዮች ዉስጥ ናቸዉ።

ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያኹ ለካቤኔያቸዉ  ” 2 ሺህ ቤተ እስራኤላውያን ወንድምና እህቶቻችንን ወደ እስራኤል ለማምጣት ትክክለኛው ግዜ አሁን ነዉ” ብለዋል።

ከተጠቀሰው ቁጥር በላይ የቀሩ ሰዎችንም ወደ ሀገሪቱ እንደሚያመጡም ጠቅላይ ሚንስትሩ ተናግረዋል።

በእስራኤል የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያን በተደጋጋሚ ኢትዮጵያ ያሉ ቤተሰቦቻቸው እንደሚመጡላቸዉ ሰልፍ በመዉጣት ጭምር ሲጠይቁ ቆይተዋል።

በአሁኑ ሰዓትም ከ 160 ሺህ በላይ ቤተ እስራኤላውያን በሀገሪቱ ይገኛሉ ተብሎ የሚገመት ሲሆን 50 ሺህ የሚድርሱት በእስራኤል የተወለዱ እንደሆነ ይነገራል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *