ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው በ20 ሺሕ ብር ዋስትና እንዲፈታ ታዘዘ

የቀድሞው የ“አል አይን ኒውስ” ጋዜጠኛ እንዲሁም “አራት ኪሎ ሚዲያ” የተሰኘው የዩቲዩብ መገናኛ ብዙሃን አዘጋጅ ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው እና የኢትዮ ሰላም የበይነ መረብ ሚዲያ መስራች ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ አስፋው ኹለቱም በ20,000 ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ ታዟል፡፡

ውሳኔውን ያስተላለፈው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ነው።

ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ሐሙስ ሚያዚያ 5/2015 ቂሊንጦ አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ማክሲኮ ወደሚገኘው ፌደራል ፖሊስ በጸጥታ ኃይሎች መወሰዱን የሚታወስ ሲሆን፤ በተመሳሳይ ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው፤ ሚያዚያ 4/2015 ምሽት ላይ ባህርዳር ከሚገኘው “ሆምላንድ ሆቴል” በጸጥታ ኃይሎች መወሰዱን መዘገባችን ይታወሳል።

ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ሲፒጂ ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን እያሰረች መሆኑን ጠቅሶ መንግሥት ያሰራቸው  ጋዜጠኞች እንዲፈታ መጠየቁ ይታወሳል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *