Womenday

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሴት ፓይለቶች ቁጥር 95 መድረሱ ተገለጸ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሴት ፓይለቶች ቁጥር 95 መድረሱ ተገለጸ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን (ማርች 8) በማስመልከት፣ በሴቶች ባለሙያዎች ብቻ የሚመሩ 8 በረራዎችን በተመሳሳይ ጊዜ ወደ ተለያዩ የአለም ሀገራትና የሀገር ውስጥ መዳረሻዎች እንደሚያከናውን ገልጿል። አየር መንገዱ ዕለቱን በማስመልከት ባከናወነው መርሃግብር ላይ እንደገለጸው ወደ ካይሮ፣ ጅቡቲ፣ ናይሮቢ፣ ፍራንክፈርት፣አክራ፣ ሙምባይ፣ ዊንድሆክ እና ድሬዳዋ የሚደረጉ በረራዎች ሙሉ በሙሉ በሴት ፓይለቶች፣ ቴክኒሻኖች እና የበረራ አስተናጋጆች የሚመሩ ይሆናሉ ተብሏል። ይህ ልዩ የበረራ መርሃ ግብር ሴቶች በአቪዬሽን ኢንዱስትሪው ውስጥ ያላቸውን አቅምና ተሳትፎ ለማሳየት ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ገልጸዋል። እንደ ዋና ስራ አስፈጻሚው መረጃ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ ካሉ ጠቅላላ ሰራተኞች መካከል 40 በመቶ ያህሉ…
Read More