16
Jul
የኢትዮጵያ ዜግነት እና ኢምግሬሽን እንዳስታወቀው ከ15 ሀገራት ዜግነት ያላቸው መንገደኞች የመዳረሻ ቪዛ እንደማያገኙ ገልጿል። ከኤርትራ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን፣ ግብፅ፣ ሊቢያ፣ ናይጄሪያ፣ ሰሜን ኮሪያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሶሪያ፣ አፍጋኒስታን፣ ኩባ፣ ዲሞክራቲክ ኮንጎ ፣ የመን እና የኢራን ዜጎች የመዳረሻ ቪዛ ወይም ቪዛ ኦን አራይቫል የማይሰጣቸው ሀገራት ናቸው። የኬንያ እና ጅቡቲ ዜጎች ግን ያለ ቪዛ ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ ተፈቅዶላቸዋል ተብሏል። የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት የተቋሙን ዓመታዊ አፈጻጸም አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ ከ1 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ቪዛ መሰጠቱን ተናግረዋል ። ተቋሙ በአንድ ዓመት ውስጥ ከአገልግሎት ፈላጊዎች 42 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡም ተገልጿል። በበጀት ዓመት 7 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሰዎች በአየር መንገዶች እና…