Propertyrights

ኢትዮጵያ የውጭ ዜጎች የቋሚ ንብረት ባለቤት እንዲሆኑ የሚፈቅድ ህግ አዘጋጀች

ኢትዮጵያ የውጭ ዜጎች የቋሚ ንብረት ባለቤት እንዲሆኑ የሚፈቅድ ህግ አዘጋጀች

የውጭ ዜጎች በኢትዮጵያ ውስጥ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት ወይም የመሬት ባለይዞታ እንዲሆኑ የሚያስችላቸው የአዋጅ ረቂቅ ተዘጋጅቷል፡፡ አዋጁ የተዘጋጀው “የዜጎችን የመሬት ይዞታ የማግኘትና የመጠቀም መብት በማያጣብብ መልኩ” እንደሆነ ተገልጿል። የውጭ ዜጎች ካፒታላቸውን “በኢትዮጵያ ስራ ላይ እንዲያውሉ ለማበረታታት” የታለመ ነው የተባለለት ይህን የህግ ረቂቅ ለፓርላማ የመራው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ነው። ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ፤ የአዋጅ ረቂቁን ጨምሮ በስድስት ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፉን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል። ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ ዜጎች የመሬት እና የንብረት ባለቤት እንዲሆኑ የሚያስችላቸው ህጋዊ አሰራር እንዲዘረጋ ከተደረገባቸው ምክንያቶች አንዱ፤ ለኢትዮጵያውያን “የስራ ዕድል ለመፍጠር ትልቅ ጠቀሜታ” ያለው በመሆኑ እንደሆነ ጽህፈት ቤቱ ገልጿል። በኢትዮጵያ የሚታየውን የመኖሪያ ቤት ፍላጎት እና…
Read More