JoeBiden

አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ጥላው የነበረውን የኢኮኖሚ ማዕቀብ አራዘመች

አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ጥላው የነበረውን የኢኮኖሚ ማዕቀብ አራዘመች

አሜሪካ ከሶስት ዓመት በፊት የተቀሰቃሰው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የአሜሪካንን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ይጎዳል በሚል ነበር ጦርነቱ እንዲቆም ጫና ስታደርግ የቆየችው፡፡ ይህ ጦርነት በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ በተደረገ የሰላም ስምምነት ቢቆምም የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ግን እንደቀጠሉ ናቸው በሚል ማዕቀቡ ተራዝሟል፡፡ በሰሜን ኢትዮጵያ እየተፈጸሙ ናቸው የተባሉት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ምስራቅ አፍሪካን እና አሜሪካንን ይጎዳል በሚል የተለያዩ እርምጃዎችን ስትወስድ ቆይታለች፡፡ በዋሸንግተን ከተወሰዱ እርምጃዎች መካከል በኢትዮጵያ ላይ ብሔራዊ የአስቸኳይ ጊዜ ማዕቀብ የሚባል ሲሆን በፈረንጆቹ መስከረም 2021 ላይ ለሁለት ዓመት የሚቆይ ማዕቀብ ተጥሎ ነበር፡፡ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ይህ ማዕቀብ ከአንድ ዓመት በፊት ለተጨማሪ አንድ ዓመት እንዲራዘም መፈረማቸው አይዘነጋም፡፡ ፕሬዝዳንቱ ፈርመውበት የነበረው…
Read More