Iranisraelwar

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የኢራንን ጥቃት አወገዙ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የኢራንን ጥቃት አወገዙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እሁድ ዕለት ኢራን በኩዌት ላይ የፈጸመችውን ጥቃት ተከትሎ ከኩዌት ልዑል አልጋ ወራሽ ሼክ ሳባህ ኻሊድ አል ሀማድ አል ሳባህ ጋር በስልክ መወያየታቸው ተገልጿል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከኩዌቱ ልዑል አልጋ ወራሽ ጋር ባደረጉት ውይይት በአገሪቱ ሉዓላዊ ግዛት እና የአየር ክልል ላይ የሚፈጸም ጥቃትን በጽኑ ማውገዛቸውን የኩዌት የዜና ወኪል ዘግቧል። ይህ በዚህ እንዳለም ኢራን በእስራኤል እና አሜሪካ በደረሰባት የአየር ላይ ጥቃት የአጸፋ እርምጃ በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ላይ በምትወስዳቸው እርምጃዎች ኢትዮጵያዊን መጎዳታቸው እየተገለጸ ይገኛል፡፡ በመቶ ሺህ የሚሆኑ ኢትዮጵያዊን እስራኤልን ጨምሮ በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ተቀጥረው በመስራት ላይ ሲሆኑ ሳውዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኢምሬት፣ ኳታር፣ ኩዌት እና ባህሬን ብዙ ኢትዮጵያዊያን ይኖራሉ፡፡ ኢራን…
Read More