Ethiopialogistics

ኢትዮጵያ የ6 መርከቦች ግዥ መፈፅሟ ተገለ

ኢትዮጵያ የ6 መርከቦች ግዥ መፈፅሟ ተገለ

የመርከቦቹ መገዛት በባህር ትራንስፖርት ላይ ያላትን አቅም የበለጠ ያሳድጋል ተብሎ ታምኖበታል፡፡ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ የሚያስተዳድራቸው 10 መርከቦች ባለቤት የሆነችው ኢትዮጵያ የማዳበሪያ ምርትን ጨምሮ የሚበዛውን ምርት የምታጓጉዘው እነዚህኑ መርከቦች ተጠቅማ ነው። አሁን ደግሞ የተጨማሪ ስድስት ትላልቅ መርከቦች ግዢ ተፈፅሞ ኢትዮጵያ መርከቦቹን ዘንድሮ እንደምትረከብ ተነግሯል። ይህም ኢትዮጵያ በውሃ ትራንስፖርት ላይ ያላትን አቅም የሚያሳድግ ነው ተብሏል። ከስድስቱ መርከቦች ሁለቱ እስከ 62,000 ቶን የመጫን አቅም ያላቸው እንደሆኑም ተነግሯል። ኢትዮጵያ አሁን ካሏት አስር መርከቦች አባይ ሁለት በመባል የምትጠራው እስከ 63,000 ቶን የመጫን አቅም እንዳላት ይነገራል። ባለፈው ዓመት ኢትዮጵያ ወደ ሀገር ውስጥ ካስገባችው 1.9 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን የማዳበሪያ ምርት አብዛኛው ተጓጉዞ ጅቡቲ ወደብ የደረሰው በራሷ መርከቦች…
Read More
ኢትዮጵያ ከ60 ሺህ ቶን በላይ እቃ የመጫን አቅም ያላትን መርከብ ተረከበች

ኢትዮጵያ ከ60 ሺህ ቶን በላይ እቃ የመጫን አቅም ያላትን መርከብ ተረከበች

ኢትዮጵያ ከ60 ሺህ ቶን በላይ እቃ የመጫን አቅም ያላትን መርከብ ተረከበች የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ በቅርቡ ባህር ዳር እና ሀዋሳ የተሰኙ ሁለት መርከቦች ለኪሳራ ዳርገውኛል በሚል መሸጡ ይታወሳል። በተሸጡት ሁለት መርከቦች ምትክም አባይ የተሰኘች አዲስ መርከብ ከቻይና መግዛቱን አስታውቋል። አዲሷ መርከብም በኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርት ታሪክ በግዙፍነቷ አቻ የላትም የተባለ ሲሆን መርከቧ በኢትዮጵያ እጅ መግባቷን ድርጅቱ አስታውቋል። የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ድርጅት በ3 ሺህ ቶን የመጫን አቅም ባላቸው መርከቦች ስራውን መጀመሩ ይታወሳል። ኢትዮጵያ የተረከበቻት አባይ የተሰኘችው አዲሷ መርከብ 63 ሺህ 229 ቶን የመጫን አቅም አላት ተብሏል። በቻይናው ያንግዡ ዳያንግ ሺፕ ቢዩልዲንግ የተገነባችው ይህች መርከብ 200 ሜትር ርዝመት እንዳላትም ተገልጿል። ይሁንና…
Read More