EthiopiaAirlines

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓመታዊ ገቢውን ወደ 25 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያሳድግ ገለጸ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓመታዊ ገቢውን ወደ 25 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያሳድግ ገለጸ

አየር መንገዱ ከ10 ዓመት በኋላ ዓመታዊ ገቢውን 25 ቢሊዮን ዶላር የማድረስ እቅድ እንዳለው አስታውቋል። ከ10 ዓመት በኋላ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ገቢ 25 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ገለጹ፡፡ አቶ መስፍን እንደገለጹት አየር መንገዱ እ.ኤ.አ በ2035 ላይ 209 ዓለም አቀፍ እና 31 የሀገር ውስጥ መዳረሻዎች፣ 271 አውሮፕላኖች እንደሚኖሩትም ጠቅሰዋል፡፡ አየር መንገዱ 67 ነጥበ 2 ሚሊዮን መንገደኞችንም በማጓጓዝ ከ10 ዓመት በኋላ ገቢውንም 25 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ መታቀዱን ገልጸዋል፡፡ ለዚህም አዳዲስ መዳረሻዎችን በማስፋት ትስስሩን ይበልጥ ማጠናከር እና አዳዲስ መዳረሻዎችን መክፈት የሚያስፈልግ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ ለዚህም አሁን በረራ ከሚደረግባቸው አምስቱ ክፍለ አኅጉሮች ተጨማሪ አውስትራሊያንም የሚጨመር መሆኑን…
Read More
የኢትዮጵያ አየር መንገድ 7 ቢሊዮን ዶላር አተረፈ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ 7 ቢሊዮን ዶላር አተረፈ

የኢትዮጵያ አየርመንገድ ግሩፕ 7 ቢሊዮን ዶላር ማትረፉን አስታውቋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በሰጠው መግለጫ በተያዘው በጀት ዓመት 7.02 ቢሊዮን ዶላር ትርፍ ማግኘቱን ገልጿል። የግሩፑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በሰጡት መግለጫ ይህ ትርፍ ከባለፈው ከመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ14 በመቶ ጭማሪ አለው ብለዋል። ትርፉ በኢትዮጵያ ብር ሲሰላ 402 ቢሊዮን ብር እንደሚሆን ስራ አስፈጻሚው ተናግረዋል። ስራ አስፈጻሚው እንደገለጹት አየርመንገዱ 577,746 የበረራ ሰአቶችን ማስመዝገቡን እና ይህም ከባለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር የ19 በመቶ ጭማሪ አለው።  በበጀት አመቱ 17.1 ሚሊዮን መንገደኞችን ማስተናገዱን የገለጸው አየር መንገዱ ከእነዚህ ውስጥ 13.4 ሚሊዮን የሚሆኑት አለምአቀፍ መንገደኞች ሲሆኑ 3.7 ሚሊዮን የሚሆኑን ደግሞ የሀገር ውስጥ መንገደኞች ናቸው ብሏል።…
Read More