Ethiokenya

ኢትዮጵያ እና ኬንያ ወታደራዊ ስምምነት ተፈራረሙ

ኢትዮጵያ እና ኬንያ ወታደራዊ ስምምነት ተፈራረሙ

ኢትዮጵያ እና ኬንያ ከ62 ዓመታት በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ ታሪካዊ የሚባል ወታደራዊ ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቱ ከሁለቱ ሀገራት ባለፈ ለቀጠናው ሰላምና መረጋጋትም የጎላ ፋይዳ ያለው መሆኑም ተገልጿል። ስምምነቱን የኢትዮጵያ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና የኬንያ መከላከያ ኢታማዦር ሹም ጄነራል ቻርልስ ሙሪዩ ካሃሪሪ ፈርመዋል። ስምምነቱ ከሃገራቱ በተጨማሪ ለቀጠናው ሰላምና ደህንነት የጎላ አስተዋጽኦ ያለው መሆኑን ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ እና የኬንያ መከላከያ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ቻርልስ ሙሪዩ ካሃሪሪ ተናግረዋል። በቀጣይም ከኢትዮጵያ መከላከያ ጋር በትብብር በሚሰሩ ስራዎች ዙሪያ የኬንያ መከላከያ በቁርጠኝነት ለመስራት ፍላጎት ያለው መሆኑን ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ቻርልስ ሙሪዩ ካሃሪሪ መናገራቸውንም ከኢኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የተገኘው መረጃ ያመላክታል። ኢትዮጵያና…
Read More
ኢትዮጵያ እና ኬንያ በሞያሌ የንግድ ልውውጥን በ1 ሺህ ዶላር ጣሪያ ለመጀመር ተስማሙ

ኢትዮጵያ እና ኬንያ በሞያሌ የንግድ ልውውጥን በ1 ሺህ ዶላር ጣሪያ ለመጀመር ተስማሙ

ኢትዮጵያ እና ኬንያ ለሁለት ዓመታት በዘለቀ ድርድር በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ማዕቀፍ የሁለትዮሽ የንግድ ልውውጥን ለማቀላጠፍ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል። በዚህም መሰረት በሞያሌ ድንበር ላይ ለሚደረጉ የሸቀጦች ንግድ የመጀመሪያ ጣሪያ 1 ሺህ የአሜሪካ ዶላር እንዲሆን ተወስኗል። በሞምባሳ የተጠናቀቀው ይህ ስምምነት የንግድ ሂደቶችን በማቅለል የድንበር ማህበረሰቦችን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ለማሳደግ ያለመ ነው። በስምምነቱ የኢትዮጵያ የድንበር ንግድ ዞን ከሞያሌ በ50 ኪሎ ሜትር እንዲሁም የኬንያ ደግሞ በ100 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚወሰን ነው። ነጋዴዎችም በጋራ በተስማሙበት የምርት ዝርዝር መሰረት እስከ 1 ሺህ የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ የንግድ ልውውጥ በወር እስከ አራት ጊዜ ድረስ ማካሄድ ይችላሉ ተብሏል። ይህ ስምምነት የንግድ ዋጋ ጣሪያዎችን፣ የጉዞ ድግግሞሽን እና የድንበር…
Read More