Digitalpayment

በኢትዮጵያ ዓመታዊ የድጅታል ገንዘብ ልውውጥ ከ18 ትሪሊዮን ብር በላይ ደረሰ

በኢትዮጵያ ዓመታዊ የድጅታል ገንዘብ ልውውጥ ከ18 ትሪሊዮን ብር በላይ ደረሰ

ብሔራዊ ባንክ እንዳስታወቀው በአንድ አመት ውስጥ በጂታል ክፍያ ስርአት 18 ነጥብ 5 ትሪሊየን ብር ዝውውር ተፈጽሟል። በኢትዮጵያ ዲጂታል ክፍያ ኮንፈረንስ 2.0. ላይ ለአምስት አመት የሚቆይ (2026-30) የብሔራዊ የዲጂታል ክፍያ ስትራቴጂ በብሔራዊ ባንክ ይፋ ሆኗል። የመጀመሪያው የ2021-24 ብሄራዊ የዲጂታል ክፍያ ስትራቴጂ ላይ ህግ ማውጣት፣ተቋማት አገልግሎቱን እንዲሰጡ ማስቻልና ቁጥጥርና ክትትል ማድረግ እንዲሁም መሠረተ ልማት ዝርጋታ መከናወናቸው ተጠቁሟል። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የክፍያ ስርአት ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ዳምጠው ለቅዳሜ ገበያ እንደገለጹት በኢኮኖሚ ዕድገት ውስጥ ትልቁ ሚና የገንዘብ ዝውውር ፈጣን ቀልጣፋ ወጪ ቆጣቢ መሆን አለበት። ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ የዲጂታል የክፍያ ስርአትን ማዘመን እና ለዚያ የሚያበቃ የድጅታል መሰረተ ልማት ግንባታ ጉልህ ሚና ይጫወታል። ባለፈው አንድ አመት…
Read More