Developmentbankofethiopia

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ዮሀንስ አያሌው ከኃላፊነት ለቀቁ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ዮሀንስ አያሌው ከኃላፊነት ለቀቁ

የልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ዮሀንስ አያሌው ስራቸውን የለቀቁት "በፈቃዳቸውና በግል ምክንያት" መሆኑን ተናግረዋል። በተጠባባቂነት የባንኩ ምክትል ፕሬዝዳን ጌታቸው ዋቄ ሀለፊነቱን እንደተረከቡ ተገልጿል። ዮሀንስ አያሌው በስራ ዘመናቸው ባንኩ ከነበረበት ውስብስብ ችግርና ክስረት  ወደ ተሻለ አቋም እንዲመለስ ማስቻላቸውን የዘርፉ ባለሙያዎች ይመስክሩላቸዋል። በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ጠለቅ ያለ እውቀት እንዳላቸው የሚነገርላቸው ዶክተር ዮሀንስ አያሌው ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክን በምክትል ገዥነት እና በዋና ኢኮኖሚስትነት አገልግለዋል። በዚህም በገንዘብ ኢኮኖሚስትነታቸው ብዙዎች የሚያደንቋቸው ሲሆን ከአምስት አመት በፊት የኢትዮጵያ ልማት ባንክን በቦርድ አባልነት አገልግለዋል፡፡ የቀድሞው የልማት ባንኩ ፕሬዝዳንት ሀይለኢየሱስ በቀለ ሲለቁ የተኩት ዮሃንስ የባንኩ ፕሬዝዳንት በመሆን ለአራት አመታት የባንኩን ፖሊሲ  መርተዋል ሲል ዋዜማ ሬዲዮ ዘግቧል። የኢትዮጵያ ልማት ባንክን ዶክተር…
Read More
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በሚሰጠው የብድር ወለድ ላይ ማሻሻያ አደረገ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በሚሰጠው የብድር ወለድ ላይ ማሻሻያ አደረገ

ባንኩ በግብርና ስራዎች ለተሰማሩ ተበዳሪዎች የብድር ወለድ መጠኑን ከ11 በመቶ ወደ 7 በመቶ ዝቅ ማድረጉን አስታውቋል። ባንኩ በኢትዮጵያ የግብርና ስራዎችን ለማበረታታት በሚል ለተበዳሪዎች በሚሰጠው ብድር ላይ ያስከፍል በነበረው ወለድ ምጣኔ ላይ ማሻሻያ ማድረጉን ገልጿል። የብድር ወለድ ቅናሽ የተደረገው ያ ያልታረሰን የመሬት ሀብት ወደ ስራ ለማስገባት፤ ባለሀብቶች፣ አርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች የበለጠ እንዲበረታቱ ለማድረግ በማሰብ እንደሆነ አስታውቋል። በዚህም መሰረት በአነስተኛ፣ መካከለኛና የኮርፖሬት ፕሮጀክት ብድር ለሚጠይቁ ይጠበቅ የነበረው የ11.5 በመቶ የማበደሪያ የወለድ ተመን ወደ 7 በመቶ ዝቅ አድርጓል ብሏል። ልማት ባንክ የሀገር ውስጥ ምርቶችን ለማሳደግ እና ከውጭ ተመርተው ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለመተካት በሚል የተቋቋመ የመንግስት የልማት ድርጅት…
Read More