Dagnewale

መንግሥት ከአማራ ክልልል ጋር በተያያዘ ታዋቂ ግለሰቦችን ሳይቀር እያሰረ እንደሆነ ተገለጸ

መንግሥት ከአማራ ክልልል ጋር በተያያዘ ታዋቂ ግለሰቦችን ሳይቀር እያሰረ እንደሆነ ተገለጸ

ከታዋቂ ሰዎች መካከል አቶ ክርስቲያን ታደለ እና ድምጻዊ ዳኜ ዋለ ዋነኞቹ ናቸው። የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) በመወከል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የኾኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ ትናንት ምሽት አዲስ አበባ ውስጥ በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደዋሉ ታውቋል። አቶ ክርስቲያን በህ/ተ/ም/ቤት ያለመከሰስ መብት ያላቸው ቢሆንም በፖሊስ ታስረዋል ተብሏል። ፖሊስ አቶ ክርስቲያንን ለምን እንዳሠራቸው ያልገለጸ ሲሆን የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባል ዶ/ር ካሳ ተሻገር እና ድምፃዊ ዳኜ ዋለም መታሰራቸው ተሰምቷል። ይህ በዚህ እንዳለም የመንግስት ኮሙንኬሽን ሚንስትርዶክተር ለገሰ ቱሉ ዛሬ በሰጡት መግለጫ በአማራ ክልል ያለውን የጸጥታ ችግር የሚያባብሱ ተናግረዋል ። ሚንስትሩ አክለውም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በዋናነት በአማራ ክልል ላይ የሚተገበር ቢሆንም፤ በየትኛው የአገሪቱ ክፍል…
Read More