17
Sep
የጣልያን ባቡር ኮርፖሬሽን ከኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል። መንግሥት በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ምክንያት የተቋረጠውን የአዋሽ- ኮምቦልቻ እና ሐራ ገበያ የባቡር መስመርን ለማጠናቀቅ ከፍተኛ ቁርጠኝነት አለኝ ብሏል። የአዋሽ- ኮምቦልቻ እና ሐራ ገበያ የባቡር መስመርን ለማጠናቀቅ ከፍተኛ የመንግስት ቁርጠኝነት ምኖሩን የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን አስታወቀ። የኮርፖሬሽኑ የህግ አገልግሎት ሃላፊ አቶ ካሳሁን ሙላቱ እንደገልፁት ኮርፖሬሽኑ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎትን ለማጠናከር ከኮይፓ ኢጣሊያ ጋር ስምምነት አድርጓል። ስምምነቱ አዳዲስ የባቡር መስመሮችን መዘርጋትን እንዲሁም እየተገነቡ ያሉ የባቡር መስመሮችን በፍጥነት አጠናቆ ወደ ስራ ማስገባትን የሚያካትት ነው ብለዋል። ከዛም ባለፈ በጋራ ድርጅቶችን ማቋቋም እንዲሁም ትላልቅ ዎርክ ሾፖሽን ማሻሻል ጨምሮ በርካታ ስትራቴጂካዊ ስራዎች የሚሰራበት የጋራ ስምምነት መሆኑን…