15
Feb
38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ በህብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ 38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ በሕብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ዛሬ መካሄድ ጀምሯል። ስብሰባው “ የማካካሻ ፍትህ ለአፍሪካውያን እና ዘርዓ አፍሪካውያን” በሚል የአፍሪካ ሕብረት ባዘጋጀው የ2025 መሪ ሃሳብ የሚካሄድ ነው። በስብሰባው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)፤ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማህማት፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ፣ የሀገራት መሪዎች እና ሌሎች ዲፕሎማቶች ተገኝተዋል። ከዛሬ ጀምሮ ለሁት ቀናት የሚመክረው የመሪዎች ጉባዔ ከሁለት ቀናት በፊት በተጠናቀቀው 46ኛው የሕብረቱ የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት በመደበኛ ስብሰባ በተለዩ አጀንዳዎች ላይ ይመክራል። ከዘንድሮው የመሪዎች ጉባዔ አጀንዳዎች መካከል የሕብረቱ ተቋማዊ ማሻሻያዎች፣ የማካካሻ…