Auction

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 60 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ጨረታ አቀረበ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 60 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ጨረታ አቀረበ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ልዩ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ነገ እንደሚያካሂድ ገልጿል፡፡ 60 ሚሊየን ዶላር በነገው ዕለት በሁሉም ባንኮች ለጨረታ እንደሚቀርብ ባንኩ አስታውቋል። ባንኩ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ፕሮግራምን ተከትሎ የኢትዮጵያ የውጭ ክፍያ ሚዛን በተለይም የወጪ ንግድ፣ ሐዋላና የካፒታል ፍሰት በከፍተኛ ደረጃ መሻሻል ማሳየቱን ጠቅሷል። በተለይም ከቅርብ ወራት ወዲህ ወርቅን ወደ ውጭ የመላክ ብቸኛ ሥልጣን ላለው ብሔራዊ ባንክ የሚቀርበው የወርቅ መጠን በመጨመሩ ምክንያት የባንኩ ዓለም አቀፍ የውጭ ምንዛሪ መጠባበቂያ ክምችት መጨመሩን ገልጿል። በመሆኑም ከባንኩ የወርቅ ግዥ ጋር በተያያዘ የሚከሰተውን የገንዘብ አቅርቦት ዕድገት ለማገናዘብና በማዕከላዊ ባንኩ እጅ ካለው ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ክምችት ከፊሉን ለግሉ ዘርፍ በመስጠት በገበያው ላይ የውጭ ምንዛሪ አቅርቦትን ለማሻሻል ባንኩ የተወሰነ…
Read More