21
Jul
የሴኔጋሉ የእግር ኳስ ኮኮብ አልሀጂ ዲዩፍ በኢትዮጵያ ላለ አንድ የስፖርት ትጥቅ አልባሳት አምራች ኩባንያ አምባሳደር ሆነው ተሹመዋል። ስምምነቱ በአዲስ አበባ የተካሄደ ሲሆን "ከአፍሪካ ምርጡ ትጥቅ አምራች ጋር ስምምነት ፈፅሜያለሁ “ ብሏል ዲዩፍ። ሴኔጋላዊው የቀድሞ ታሪካዊ ተጨዋች ኤል ሀጂ ዲዩፍ የኢትዮጵያው ትጥቅ አምራች ብራንድ ዋናው አምባሳደር በመሆን መሾሙን ኩባንያው ገልጿል። ታሪካዊው ተጫዋች የዋናው ስፖርት አልባሳት በሚመረትበት አዲስ አበባ ሀብቴ ጋርመንት እና ህትመትን ከጎበኘ በኋላ ስምምነት ፈፅሟል። “ ከአፍሪካ ምርጡ ትጥቅ አምራች ጋር ስምምነት ፈፅሜያለሁ “ ሲል ዲዩፍ ከጉብኝቱ በኋላ ተናግሯል። አክሎም "በቀጣይ ከትልልቅ ታሪካዊ ተጫዋቾች ጄጄ ኦኮቻ ፣ ኑዋንኩ ካኑ ፣ አዲባየር እና ካሊዱ ፋዲጋን በማምጣት ዋናውን በአለም ገናነቱን እናሳየለን "…