13
Feb
ሁለተኛው የአፍሪካ-ጣሊያን መሪዎች ጉባኤ ለመጀመሪያ ጊዜ ከጣሊያን ዋና ከተማ ሮም ውጭ በአፍሪካ ምድር በአዲስ አበባ አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ዛሬ መካሄድ ጀምሯል። ይህ ጉባኤ የጣሊያንና አፍሪካ ግንኙነት በአህጉራዊና በዓለም አቀፋዊ ትብብሮች ይበልጥ እንዲጠናከር የሚያደርግ ሲሆን፣ ኢትዮጵያም አህጉሪቱን ከተቀረው ዓለም ጋር ለማስተሳሰር ያላትን የዲፕሎማሲ አቅም በተግባር ያሳየችበት መድረክ ሆኗል። በጉባኤው ላይ የሀገራት መሪዎች እና የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝን ጨምሮ የዓለም አቀፍ ተቋማት ኃላፊዎች ተገኝተዋል። ታሪካዊው ስብሰባ በፈረንጆቹ 2024 በሮም የቀረበውን የጣሊያን "የማቲ ዕቅድ" (Mattei Plan) አፈጻጸም የሚገመግም ሲሆን፣ በተለይም በሀይል ልማት፣ በግብርና፣ በትምህርት እና በጤና ዘርፎች ላይ ያተኮረ ሰፊ ምክክር ያደርጋል። የመንግሥት ኮምኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ደኤታ አቶ ተስፋሁን…