27
May
57 በመቶ የሚሆኑት የአፍሪካ ሀገራት ለከፍተኛ የእዳ ችግር መጋለጣቸው ተገልጿል። እነዚሁ ታዳጊ ሀገራት በተያዘው ዓመት ብቻ ከ 80 ቢሊዮን ዶላር በላይ የዉጪ እዳ እንዲከፍሉ ይጠበቃል በአፍሪካ የሕዝብ ዕዳ ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የአፍሪካ ኢንሹራንስ ድርጅት አስታውቋል ። እንደ ድርጅቱ መረጃ ከሆነ በአህጉሪቱ ከሚገኙ ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት መካከል 57% የሚሆኑት በዕዳ ችግር ውስጥ ገብተዋል ወይም ከፍተኛ የዕዳ ስጋት ላይ ይገኛሉ። ይህንን አኃዝ የገለጹት የድርጅቱ ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ፓቲ ማርቲን በአዳስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘዉ 51ኛዉ የአፍሪካ ኢንሹራንስ ድርጅት ዓመታዊ ኮንፍረንስ እና ጠቅላላ ጉባኤ መድረክ ላይ ሲሆን :- በዚህ ንግግራቸው የዕዳው ጫና መጨመር ዋና ዋና መንስኤዎች የዓለም አቀፍ የገበያ መዋዠቅ እና…