Addisstandard

አዲስ ስታንዳርድ ሚዲያ ፈቃድ መሰረዙ ተገለጸ

አዲስ ስታንዳርድ ሚዲያ ፈቃድ መሰረዙ ተገለጸ

የኢትዮጵያ  መገናኛ ብዙሀን ባለስልጣን እንዳስታወቀው የአዲስ ስታንዳርድ የበየነ-መረብ መገናኛ ብዙኃን ምዝገባ ምስክር ወረቀት ከየካቲት 17 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ  ተሰርዟል ብሏል፡፡ እንደ ባለስልጣኑ መግለጫ ከሆነ አዲስ ስታንዳርድ የበየነ-መረብ መገናኛ ብዙኃን የሚዲያ ስነ ምግባርን፣ የኢትዮጵያ ሕጎች እና የሀገርንና የሕዝብን ብሔራዊ ጥቅም አደጋ ላይ የሚጥሉ ዘገባዎችን በተደጋጋሚ በማሰራጨት ላይ ይገኛል ሲል አስታውቋል፡፡ በመሆኑም ባለሥልጣኑ ይህንኑ ድርጊት በመመርመር አዲስ ስታንዳርድ የበይነ መረብ መገናኛ ብዙኃን እንዲታረም እና ከአጥፊ አካሄዱ እንዲቆጠብ በተደጋጋሚ ምክር ሲሰጥ ቢቆይም ለመታረም ፈቃደኛ ሳይሆን በመቅረቱ ፈቃዲ እንደተሰረዘ ባለስልጣኑ ገልጿል። በተጨማሪም በሚዲያ ዘርፉ ላይ የሙያ ስነምግባር እና የሀገርና የህዝብ ብሔራዊ ጥቅም አክብሮ እንዲሰራ ተደጋጋሚ ማሳሰቢያ እና ማስጠንቀቂያ ቢሰጠውም ለመታረም ፈቃደኛ አልሆነም ያለው…
Read More