abyssiniabank

አቢሲንያ ባንክ ሰባት ቢሊዮን ብር ማትረፉን ገለጸ

አቢሲንያ ባንክ ሰባት ቢሊዮን ብር ማትረፉን ገለጸ

አቢሲንያ ባንክ አጠቃላይ ሀብቱ ከ286 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን አስታውቋል። አቢሲንያ ባንክ በዛሬው ዕለት ዓመታዊ የባለአክስዮኖች 29ኛ መደበኛ እና 16ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤው አካሂዷል። በጉባኤው ላይ እ.ኤ.አ በ2024/25 የሒሳብ ዓመት ሪፖርት የቀረበ ሲሆን፤ የባንኩ አጠቃላይ ሀብት 286 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር መድረሱን አስታውቋል፡፡ ይህም ካለፈው ዓመት አጠቃላይ ሀብት ማለትም ከ222 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ጋር ሲነጻጸር የ63 ነጥብ 9 ቢሊዮን ወይም የ28 ነጥብ 8 በመቶ ዕድገት ማሳየቱን የአቢሲኒያ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር አቶ መኮንን ማንያዘዋል ገልጸዋል። ባለፈው የሒሳብ ዓመት የባንኩ ጠቅላላ ገቢው 39 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር መድረሱን የገለጹ ሲሆን፤ ውጤቱ ካለፈው ተመሳሳይ ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ11 ነጥብ 3 ቢሊዮን…
Read More
የአዳማ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች የአንድ ሚሊዮን ብር ሽልማት አሸነፉ

የአዳማ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች የአንድ ሚሊዮን ብር ሽልማት አሸነፉ

አቢሲኒያ ባንክ ለሶስት እንስቶች አንድ ሚሊዮን ብር ሸለመ ባንኩ "አሚን አዋርድ" በሚል የሰየመውን የሥራ ፈጠራ ውድድር አጠናቋል፡፡ ውድድሩ ካሳለፍነው ህዳር ጀምሮ ሲካሄድ የቆየ በሥራ ፈጠራቸው ይዘት እና ችግር ፈቺነታቸው ለተመረጡ 5 ተወዳዳሪዎች የእውቅናና የሽልማት መርሐ-ግብር በአዳማ ከተማ ተካሂዷል፡፡ በውድድሩ ላይ ከ1ኛ - 5ኛ ለወጡ ተሳታፊዎች በአጠቃላይ 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የተሸለሙ ሲሆን ከ6ተኛ እስከ 20ኛ ድረስ ለወጡ ተሳታፊዎችም የማበረታቻ ሽልማት መሰጠቱን አቢሲኒያ ባንክ ለኢትዮ ነጋሪ በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡ የአንደኝነት ደረጃን በማግኘት የ1,000,000 ብር ተሸላሚ የሆኑት በአዳማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የነበሩ ሦስት እንስቶች አሸንፈዋል፡፡ እንስቶቹ ‹ግሪን ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ማዳበሪያ› በሚል በጋራ ባቋቋሙት ድርጅት ስም አሸናፊ በመሆን ሽልማቱ ተበርክቶላቸዋል፡፡
Read More