ሹመት

የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ሹመት ተቃውሞ ገጠመው

የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ሹመት ተቃውሞ ገጠመው

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው መደበኛ ጉባኤ የአምስት ሚንስትሮችን ሹመት ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ውሳኔ አሳልፏል። ለምክር ቤቱ ከቀረቡ አጀንዳዎች መካከል የአምስት ሚንስትሮች ሹመት አንዱ ሲሆን የምክር ቤት አባላት እና የመንግስት ተጠሪ ክርክር አድርገዋል። ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ከሁለት ሳምንታት በፊት የሾሟቸው አምስት ሚንስትሮች በዛሬው የምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ የቀረበ ሲሆን የምክር ቤት አባላት በሹመቱ ዙሪያ ጥያቄ አንስተዋል። ከተነሱ ጥያቄዎች መካከልም የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ተደርገው የተሾሙት እና ስራ የጀመሩት ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) አንዱ ነበር። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ወክለው የምክር ቤቱ አባል የሆኑት ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ጥያቄ ካነሱት መካከል አንዱ ነበሩ። ሹመቱን አስመልክቶ ካነሱት ጥያቄ መካከልም "የፍትህ…
Read More
ጌዲዮን ጥሞቲዮስ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ሆነው ተሾሙ

ጌዲዮን ጥሞቲዮስ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ሆነው ተሾሙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ለተለያዩ ተቋማት አዳዲስ ሚኒስትሮችን ሾመዋል። በዚህም መሰረት ጌዲዮን ጥሞቲዮስ (ዶ/ር) በቅርቡ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ተደርገው በተሾሙት ታዬ አጽቀስላሴ ምትክ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ሆነው ተሾመዋል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሹመት በተጨማሪም ወ/ሮ ሃና አርአያስላሴ የፍትህ  ሚኒስትር ሆነው ተሾመዋል። ወ/ሮ ሃና አርዓያሥላሴ ፍትህ ሚኒስትር ተደርገው ከመሾማቸው በፊት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር እንዲሁም ከዚያ በፊት የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ዳይሬክተር ሆነው ሲያገለግሉ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡ እንዲሁም የመንግስት ኮሙንኬሽን ምክትል ሚኒስትር የነበሩት ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ የቱርዝም ሚንስትር ተደርገው መሾማቸውንም ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ደኤታ በመሆን በማገልገል ላይ የነበሩት ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ፤…
Read More