የሩሲያ መኪና አምራች ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ኢንቨስት ሊያደርጉ መሆኑን ገለጹ

የሩሲያ  የመኪና አምራች ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ጉብኝት በማድረግ ላይ ሲሆኑ በድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጠና ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡

ከሩሲያ የላዳ እና ጋዝ ግሩፕ መኪና አምራች ኩባንያዎች የመጡ ተወካዮች ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሽፈራው ሰለሞን ጋር ተወያይተዋል፡፡

ለተወካዮቹ  በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ያለውን ምቹ የኢንቨስትመንት ሁኔታ፣ ስለዘርፉ ማበረታቻዎች እንዲሁም በአፍሪካ ግንባር ቀደም ስለሆነው የድሬዳዋ የነጻ ንግድ ቀጠና አጠቃላይ ገለጻ ተደረገላቸዋል፡፡

የመኪና አምራች ኩባንያ ኃላፊዎቹ ከድሬዳዋ በተጨማሪ የቦሌ ለሚ እና ቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን የስራ እንቅስቃሴና የምርት ሂደት ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡

ኩባንያዎቹ በአውሮፓ፣ በደቡብ አሜሪካና የአፍሪካ ገበያዎች ለጤና ተቋማት፣ ለፀጥታ አካላት፣ ለጭነት አገልግሎት እንዲሁም ለግልና ለህዝብ ትራንስፖርት ዘርፍ የሚውሉ የተለያየ ሞዴል  ያላቸው ተሽከርካሪዎችን በማቅረብ ታዋቂ መሆናቸው  ይታወቃል።

ተወካዮቹ በተለይም በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና ኢንቨስት በማድረግ የተለያዩ ምዴል ምርቶችን  በኢትዮጵያ ገበያ የማቅረብ ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል ።

ሩሲያ በኢትዮጵያ የመኪና ኢንዱስትሪ ውስጥ ቀድመው የሚታወቁ ሲሆን በተለይም ላዳ የተሰኘችው መኪና ሞዴል በኢትዮጵያ ከተሞች የተለመዱ ናቸው፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *