ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የማህበራዊ ትስስር ኩባንያዎች ቢሯቸውን በአዲስ አበባ እንዲከፍቱ ጠየቀች

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን እንደ ሜታ (ፌሰቡክ) ያሉ የማኅበራዊ ትስስር አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ቅርጫንፍ ቢሮዎቻቸውን በኢትዮጵያ እንዲከፍቱ ጠይቋል፡፡

ባለሥልጣኑ በበይነ መረብ የሚካሄዱ የጥላቻ ንግግችን የሚመለከት የአንድ ዓመት ሪፖርቱን የተመለከተ መግለጫ ለመገናኛ ብዙኃን ሰጥቷል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን “እንደ ፌስቡክ ያሉ ድርጅቶች ከፍተኛ ተጠቃሚ ባለው ኢትዮጵያ ለማስታወቂያ ገቢ እያስገኙ አይደለም” ብሏል።

ኢትዮጵያ ከ44 ሚሊዮን በላይ የበይነ ተጠቃሚዎች ያሉባት ሀገር ብትሆንም፤ እስካሁን ድረስ የማኅበራዊ ሚዲያ ፖለሲም ሆነ አዋጅ የላትም።

ባለሥልጣኑ ለሦስተኛ ግዜ እንዳዘጋጀው በተገለጸው ሪፖርት ላይ፤ የጥላቻ ንግግር ከምንጊዜውም በላይ በበይነ መረብ አማካኝነት መስፋፋቱን ያሳያል ብሏል።

ከጥር 2016 ዓ.ም. እስከ ጥር 2017 ዓ.ም. ያለውን የአንድ ዓመት ሪፖርት መቅረቡን ለመገናኛ ብዙኃን የገለጹት መግለጫውን የሰጡት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አማካሪ ታምራት ደጀኔ ናቸው።

አቶ ታምራት እንደ ሜታ ያሉ ትልልቅ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች በጎረቤት ሀገራት ሳይቀር ቅርጫፍ ቢሮ እንዳላቸው የገለጹ ሲሆን፤ “ከፍተኛ ተጠቃሚ ባላት ኢትዮጵያ እስካሁን ቅርጫፍ ቢሮ አለመኖሩ ተገቢ አይደለም” ብለዋል።

ኩባንያዎቹ የኢትዮጵያ ጥቅም ባስጠበቀ መልኩ እንዲሰሩ መታሰቡን አቶ ታምራት ገልጸው፤ የማኅበራዊ ሚዲያ መመሪያ ፖሊሲ በአዋጅ ተደግፎ በዝርዝር እንዲወጣ መታሰቡንም አስታውዋል።

ሌሎች ሀገራት ላይ የማኅበራዊ ሚዲያ ተቋማት ከፍተኛ የሆነ ገቢ ከማስታወቂያ እንደሚያስገቡ የገለጹ ሲሆን፤ “ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ከሚያገኙት የማስታወቂያ ገቢ እያስገኙ ባለመሆኑ ይህንን እንዲያስገቡ ይጠበቃል” ሲሉ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ወደ 4 ሚሊዮን የሚሆን የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ ቢኖራትም፤ አጀንዳ በማስቀየር ደረጃ ከፍተኛ የሆነ አቅም ያላቸው ተጠቃሚዎች እንዳሏት በአንድ ዓመቱ ጥናት ተመላክቷል።

ጥናቱ በዋናነት እንደ ፌስቡክ፣ ቲክቶክ፣ ቴሌግራም፣ ዩትዩብ እና ኤክስ (ትዊተር) በመሳሰሉ ከፍተኛ ተጠቃሚ ባላቸው ማኅበራዊ ሚድያ አውታሮች ላይ የተደረገ ሲሆን፤ የመረጃ ምንጮቹም ከ5 ሺሕ በላይ ተጠቃሚ ያላቸው የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች መሆናቸው ተረጋግጧል።

በከፍተኛ ሁኔታ ጥላቻ ንግግር የሚዘዋወረው በአብዛኛው በጽሑፍና በተንቀሳቀሽ ምስሎች መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ በአብዛኛው ደግሞ በፌስቡክ፣ በቴሌግራም እና ቲክቶክ መሆኑ ተገልጿል።

ኢትዮጵያ የሐሰተኛ እና ጥላቻ ንግግር ለመከላከል በማሳብ በባለስልጣኑ ይህንን ጥናት ሲያደርግ ለሦስተኛ ጊዜ ቢሆንም ጥፋቱ እየጨመረ እንጂ መቀነስ አለማሳቱ ተነግሯል።

ባለስልጣኑ የማኅበራዊ ሚዲያ ፖሊሲም ሆነ አዋጅ ሳያዘጋጅ ተቋማቱ በምን አግባብ ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ እንደጠየቅ፤ በቂ መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።

ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት እንደ ጎግል እና መሰል ኩባንያዎች ታክስ እንዲከፍሉ የሚያስገድድ መመሪያ በማዘጋጀት ላይ መሆኗን አስታውቃ ነበር።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *