የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ14 ሚሊዮን በላይ መንገደኞች ማጓጓዙን ገለጸ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለፉት 9 ወራት 14.5 ሚሊዮን መንገደኞችን ማጓጓዙን አስታውቋል፡፡

ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከር የ13 በመቶ እድገት እንዳለው ዋና ስራ አስፈፃሚው መስፍን ጣሰው ተናግረዋል፡፡

አየር መንገዱ በዘጠኝ ወር ውስጥ ያገኘው ገቢ 5.6 ቢሊዮን ዶላር መሆኑንን የተናገሩት አቶ መስፍን ጣሰው ገቢውም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲተያይ የ8 በመቶ ብልጫ አሳይቷል ብለዋል፡፡

በጊዜ ማዕቀፍ 10 አዳዲስ አውሮፕላኖች የኢትዮጵያ አየር መንገድን መቀላቀላቸው የተጠቀሰ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ሶስቱ ኤርባስ A350-1000 መሆናቸው ተሰምቷል፡፡

በዘጠኝ ወሩ ውስጥ አራት አዳዲስ የበረራ መዳረሻዎችንም የኢትዮጵያ አየር መንገድ መክፈቱን ጠቅሷል፡፡

አየር መንገዱ የፊታችን እሁድ ጁን 1, 2025 ከአዲስ አበባ ወደ ተባበሩት አረብ ኢምሬት ሻርጃህ ከተማ የቀጥታ በረራ እንደሚጀምር አስታውቋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመጪው ሰኔ ወር ብቻ ሁለት አለም አቀፍ በረራዎችን እንደሚጀምር እንዲሁም ሁለት ኤር ባስ A350-900 አውሮፕላኖችን እንደሚረከብ አቶ መስፍን አስረድተዋል፡፡

በቢሾፍቱ ለሚገነባው ግዙፍ ኤርፖርት የዝግጅት ስራ እየተሰራ መሆኑንን የተናገሩት ዋና ስራ አስፈፃሚ የኤርፖርቱን ግንባታ በመጪው ዓመት ህዳር ወር ለመጀመር ታስቧል ብለዋል፡፡

በዓመት 100 ሚሊዮን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም ያለው ይህ አውሮፕላን ጣቢያ ወይም ኤርፖርት የሚገነባው በዓመት 25 ሚሊዮን መንገደኞችን ብቻ የማስተናገድ ያለው ቦሌ ዓከም አቀፍ ኤርፖርትን ለመተካት እንደሆነ የተቋሙ ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ተናግረዋል።

በቢሾፍቱ ልዩ ስሙ አቡ ሴራ በተባለው ስፍራ የሚገነባው ይህ ኤርፖርት ግንባታ ዲዛይን ዳር የተሰኘው ኩባንያ መመረጡንም አቶ መስፍን ገልጸዋል።

አቶ መስፍን አክለውም አዲሱ ኤርፖርት ግንባታ በአምስት ዓመታት ውስጥ በሁለት ዙር ይገነባል ያሉ ሲሆን ለመጀመሪያው ዙር ግንባታ ስድስት ቢሊዮን ዶላር ወጪ ይደርግበታልም ብለዋል።

ኤርፖርቱ ባንድ ጊዜ አራት አውሮፕላኖችን የማሳረፍ እና መንደርደሪያ መም ይኖረዋል ተብሏል።

270 አውሮፕላኖችን የማሳረፍ አቅም ያለው አዲሱ ኤርፖርት ከቦሌ ኤርፖርት ጋር የሚያስተሳስር ፈጣን ባቡር እና መንገድ እንደሚገነባም ተገልጿል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *