ብሔራዊ ሎተሪ 50 ሚሊዮን ብር የሚያሸልም ሎተሪ ይፋ አደረገ

የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት እንደገለፀው ይህ ዘመናዊ ሎተሪ ከወረቀት ሎተሪ በተጨማሪ በዲጅታል መላ በሞባይል መተግበሪያ አማካኝነት አገልግሎት የሚሰጥ ነው ብሏል።

በዲጂታል ሎተሪ ለረጅም ዓመታት በመፋቅ እድለኛ የሚያደርጉት የፈጣን እና የቢንጎ ሎተሪዎችም በዲጅታል መንገድ እንደተካተቱ ተገልጿል።

ከሀምሳ ሚሊዮን ብር ሽልማት አንስቶ በርካታ የጨዋታ አማራጮችን የቀረበበት  ሲሆን በስምንት የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ተዘጋጅቷል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሎተሪ አገልግሎት ይህንን የዲጂታል ሽግግር ለማሳካት ታምኮን ሶፍትዌር ሶሉሽንስ ከተባለ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ጋር  እየሰራ መሆኑን ገልጿል።

አገልግሎቱ በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከዲጅታል ሎተሪ በተጨማሪ በሃምሳ ሺህ ብር ሽልማት የከፈተውን የእድል በር ወደ ሃምሣ ሚሊየን ብር ከፍ ለማድረግ እንደበቃም ተናግሯል።

ብሔራዊ ሎተሪ በየጊዜው አዳዲስ የሎተሪ እድኮችን ለደንበኞቹ ያስተዋወቀ ሲሆን ከሁለት ዓመት በፊት አድማስ ድጅታል ሎተሪን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

አድማስ ድጅታል ሎተሪ ከመስከረም 2015 ዓ.ም ጀምሮ ለአንደኛ አሸናፊ አንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር በመሸለም ነበር ስራ የጀመረው፡፡

በመቀጠልም የሽልማት መጠኑን ወደ ሶስት ሚሊዮን ብር ከፍ የተደረገው አድማስ ድጅታል ሎተሪ ደንበኞች የእጅ ስልካቸውን በመጠቀም በሶስት ብር እና በአምስት ብር የሎተሪ እጣ የሚቆርጡበት የሎተሪ ስርዓት ነው፡፡

በደምበኞች አስተያየት መሰረት ቀደም ሲል የነበበረውን የዕጣ ሽልማት የአንደኛው ዕጣ 4 ሚሊዮን ብር፣ የሁለተኛው ዕጣ 2 ሚሊዮን ብር የሶስተኛው ዕጣ 1 ሚሊዮን ብር በማድረግ ተደርጓል ተብሏል፡፡

ከ60 ዓመት በፊት ስራ የጀመረው ብሔራዊ ሎተሪ የሎተሪ እድሎችን በቁጥር እና በሽልማት መጠን በየጊዜው እያሳደገ አሁንም ቀጥሏል።

አስተዳድሩ አሁን ላይ 14 አይነት የሎተሪ እድል መሞከሪያ እጣዎች ያሉት ሲሆን ቶምቦላ፣ ዝሆን፣ እንቁጣጣሽ፣ ትንሳኤ፣ የገና ስጦታ፣ ልዩ፣ ቢንጎ፣እና ፈጣን ዋነኞቹ ናቸው።

አሁን ላይ ተቋሙ ከ15 እስከ ሁለት ወራት የሚቆዩ የሎተሪ አሸናፊ እጣዎች ያሉት ሲሆን ለባለ እድለኞች እስከ 50 ሚሊዮን ብር ድረስ በመሸለም ላይ ይገኛል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *