የብሪታንያው ግሪን ሞሽን የመኪና ኪራይ ኩባንያ በኢትዮጵያ ስራ ጀመረ

ኢትዮዽያ የእንግሊዙን ግሪን ሞሽን የመኪና ኪራይ አገልግሎት ሰጪ ኩባንያ ወደ አዲስ አበባ መምጣቱ ተገልጿል።

ዋና መስሪያ ቤቱን በእንግሊዝ ያደረገው ግሪን ሞሽን የመኪና ኪራይ አገልግሎት አቅራቢ ኢትዮጵያን  80ኛ መዳረሻው በማድረግ ስራ መጀመሩ ተሰምቷል።

ግሪን ሞሽን ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጣ ያደረገው በመኪና ኪራይ ዘርፍ ላለፉት 10 ዓመታት ሲሰራ የቆየው ኤክሰለንት የመኪና ኪራይ ድርጅት ነው፡፡

ስራውን በአዲስ አበባ እውን ለማድረግ ሁለት ዓመት የፈጀ ድርድር ሲደረግ ቆይቷል ተብሏል፡፡

በተለይ ኢትዮጵያን ለመጎብኘት የሚመጡ ሰዎች ለስብሰባ ለመሳሰሉት ጉዳዮች አዲስ አበባን የሚረግጡ ተጓዦች በቆይታቸው የመኪና ኪራይ የሚያስፈልጋቸው ከሆነ ገና ከመምጣታቸው አስቀድሞ የመኪና አይነቱንም ክፍያውንም መፈፀም እንደሚችሉ ተናግሯል።

ይህ በመሆኑም የሀገርን ገፅታ ከፍ ያደርጋል የውጭ ምንዛሪ ግኝትንም ለመፍጠር እድል ነው ተብሏል።

የአገልግሎት ተጠቃሚዎች ከየትኛውም አለም በግሪንሞሽን ኢትዮጵያ ድረ ገፅ እና መተግበሪያዎች በመግባት የመኪና ኪራይ ውል ማሰር እና በተቀመጠው አማራጮችም ክፍያ መፈፀም ይችላሉ ተብሏል፡፡

ዋና አገልግሎቱ ለቢዝነስ፣ ለስብሰባ፣ ለጉብኝት ለመሳሰሉ ከውጭ ሀገር ለሚመጡ ሰዎች ቢሆንም ሀገር ውስጥ ያሉ ደንበኞቹን እንደሚያስተናግድ ተገልጿል፡፡

በኤክሰለንት የመኪና ኪራይ በኩል ግዙፉ ግሪን ሞሽን ወደ ኢትዮጵያ መምጣቱ በተለይ ለቱሪዝሙ ከፍተኛ ጥቅም እንደሚኖረው የባሕል እና ቱሪዝም ሚኒስትር ድኤታ እንደገና አበበ ተናግረዋል፡፡

የግሪን ሞሽን ኢትዮዽያ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብዙአየሁ ታደሰ በንግግራቸው ግሪን ሞሽን በኢትዮዽያ ስራ መጀመሩ ለሀገር ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ከማምጣትም ባለፈ በጎ ገፅታዋን ለአለም ለማሳየት እድሉን ይከፍትላታል ብለዋል።

የግሪን ሞሽን  ኢትዮዽያ አለም በእጅጉ የሚያስፈልጋትን ለአየር ንብረት ለውጥ በጎ አስተዋፅኦ በሚያደርጉ አሰራሮች መቃኘቱ ለኢትዮዽያ ያግዛል ብለዋል።

አቶ ብዙአየሁ ይህ አለም አቀፍ ኩባንያ ወደ ሀገራችን አምጥተን አገልግሎት በማስጀመራችን ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያስገኝልናል፤ ከነዚህም ውስጥ የእውቀት ሽግግር፣ የውጭ ምንዛሪ ፍሰት፣ የስራ እድል፣ የአካባቢ ጥበቃ እና የእንግዶች እርካታ ዋነኞቹ ናቸው ብለዋል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *