ኩባንያው በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ለዘመድ አዝማድ የሚልኩትን ገንዘብ (ሪሚታንስ) በማስተላለፍ አገልግሎት ላይ ለመሠማራት ማቀዱን አስታውቋል።
ኩባንያው በዘርፉ መሠማራት የፈለገው፣ የውጭ ምንዛሬ ፖሊሲ ለውጡ በመደበኛውና በትይዩ ገበያው መካከል ያለውን የምንዛሬ ልዩነት ማጥበቡን ተከትሎ ነው
ኩባንያው፣ ኬንያና ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በሪሚታንስ አስተላላፊነት ዘርፍ የተሰማራ ሲሆን ከዓለማቀፉ ገንዘብ አስተላላፊ ኩባንያ ዳሃብሺል ጋር ባለፈው ሐምሌ የመግባቢያ ስምምነት መፈራረሙ ይታወሳል።
የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሞባይል ፋይናንስ አገልግሎት የሆነው ኤምፔሳ (M-PESA) ከአንድ ዓመት በፊት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የአገልግሎት ፍቃድ ካገኘ ከሦስት ወራት በኋላ ስራ መጀመሩ አይዘነጋም።
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በቀጣዮቹ ሶስት ዓመታት ውስጥ ለኔትወርክ ማስፋፊያ 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር መድቤያለሁ ብሏል፡፡
ተቋሙ አክሎም በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎችበተጠቀሱት ዓመታት ውስጥ 5 ሺህ አዳዲስ የኔትወርክ ማማዎችን እንደሚተክልም አስታውቋል፡፡
ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በተደረገ የሁለትዮሽ ስምምነት የኔትወርክ አገልግሎቱን ለደንበኞቹ እየሰጠ መሆኑን ያሳወቀው ሳፋሪ ኮም ቀስ በቀስ የራሱን የኔትወርክ መስመሮች እየገነባ እንደሆነም ገልጿል፡፡
አሁን ላይ ድርጅቱ በ2 ሺህ 500 የኔትወርክ ማማዎች አገልግሎት እየሰጠሁ ነው የሚለው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከዚህ ውስጥ 1 ሺህ 500 ያህሉ ራሴ የገነባኋቸው ናቸውም ብሏል፡፡
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የቴሌኮም አገልግሎት ነሀሴ 2014 ዓ.ም ላይ በድሬዳዋ ማስጀመሩ ይታወሳል፡፡
ድርጅቱ በቀጣዮቹ ሶስት ዓመታት ውስጥ ለ50 በመቶ ህዝብ እንዲሁም በቀጣዮቹ አስር ዓመታት ውስጥ ደግሞ 98 በመቶ ለሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን የቴሌኮም አገልግሎት የመስጠት እቅድ እንዳለው አስታውቋል።
ሳፋሪኮም ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ቮዳኮም ግሩፕ፣ ቮዳፎን ግሩፕ፣ ሱሚቶሞ ኮርፖሬሽንና ሲዲሲ ግሩፕን ያካተተ ነው።