ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ሁለተኛውን ዙር ድርድር በአንካራ ጀመሩ

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ከወደብ ጋር በተያያዘ በመካከላቸው የተፈጠረዉን ዉጥረት ለመፍታት ሁለተኛ ዙር ድርድራቸውን በአንካራ ጀምረዋል፡፡

የቱርክ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይፕ ኤርዶሃን በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ንትርክ ዙሪያ ከፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ጋር በስልክ መምከራቸውም ተሰምቷል፡፡

የቱርክ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይፕ ኤርዶሃን ከሶማሊያ አቻቸዉ ሀሰን ሼክ ማህሙድ ጋር በስልክ መምከራቸዉ ተዘግቧል።

በቱርክ እና በሶማሊያ መካከል ያለውን ትብብር አስፈላጊነት በማጉላት አንካራ ፥ በሞቃዲሾ እና በአዲስ አበባ መካከል ያለውን አለመግባባት ለመፍታት ጥረቷን እንደምትቀጥል የቱርክ ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በኤክስ ገጹ ላይ ጽፏል።

በዛሬዉ እለት በቱርኪዬ ርዕሰ መዲና አንካራ ከሚካሄደው ሁለተኛ ዙር የሶማሊያ እና የኢትዮጵያ ድርድር ውጥረቱን ለማርገብ ተጨባጭ ውጤት ይጠበቃል ብሏል።

መሪዎቹ በስልክ ዉይይታቸዊ በሁለትዮሽ ግንኙነት እንዲሁም በአህጉራዊ እና አለምአቀፋዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ዳይሬክቶሬቱ አክሎ ገልጿል።

ይህ የተሰማዉ ባለፈው ቅዳሜ የቱርኩ ፕሬዚዳንት ኤርዶጋን እና የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የስልክ ዉይይት ካደረጉ በኋላ ነዉ ተብሏል። ኤርዶሃን ከጠ/ሚኒስትር ዐቢይ ጋር በዉይይታቸዉ የእርቅ ጉዳይ ዋናዉ አጀንዳም ነበር ተብሏል።

ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ተገንጣይ ግዛት ጋር የባህር በር ለማግኘት ስምምነት ካሰረች በኋላ በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል ዉጥረት ተፈጥሯል።

ቱርክ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ውጥረት ለማርገብ እና ለማነጋገገር ጥረት ስታረግ የቆየች ሲሆን በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች መካከል የመጀመሪያ ዙር ቀጥተኛ ውይይት ባሳለፍነው ሰኔ ወር ላይ ማዘጋጀቷ አይዘነጋም።

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያም ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ወደ አንካራ ያቀኑ ሲሆን ከቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሀካን ፊዳን ጋር የተገናኙ ሲሆን ውይይት እንደቀጠለ ነው ተብሏል፡፡

ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር 20 ኪሎሜትር ርቀት ያለዉ የባህር በር የምታገኝበትን ስምምነት ባሳለፍነው ጥር ወር ላይ በአዲስ አበባ ተፈራርመው ነበር።

ሶማሊያ ለኢትዮጵያ ወደብ ለመስጠት ፈቃደኛ ስትሆን ኢትዮጵያ ደግሞ ከራስገዟ ሶማሊላንድ ጋር ያደረገችውን የባህር በር ስምምነት እንድትቀድ ቅድመ ሁኔታ አስቀምጣለች፡፡

ይሁንና ኢትዮጵያ ሶማሊያ ያቀረበችላትን ሀሳብ ስለመቀበሏም ሆነ መቃወሟን በይፋ እስካሁን አላሳወቀችም፡፡

ሶማሊያ ከቱርክ ጋር ለ10 ዓመት የሚቆይ ወታደራዊ ስምምነት የተፈራረመች ሲሆን በዚህ ስምምነት መሰረት የቱርክ ባህር ሀይል የሶማሊያ ወደቦችን እና ባህርን ይቆጣተራል፡፡

የሶማሊያ ግዛት አካል አይደለሁም የምትለው ሶማሊላንድ በበኩሏ ከቱርክ ጋር የተደረገው ወታደራዊ ስምምነት እንደማይመለከታት አስታውቃለች፡፡

By New admin

One thought on “ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ሁለተኛውን ዙር ድርድር በአንካራ ጀመሩ

  • Hello, Jack speaking. I’ve bookmarked your site and make it a habit to check in daily. The information is top-notch, and I appreciate your efforts.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *