ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በትግራይ የቴሌኮም አገልግሎት ሊሰጥ መሆኑን አስታወቀ

Safaricom in Tigray

ሳፋሪኮም በትግራይ ክልል የኔትወርክ እና መሠረት ልማት ዝርጋታ በሚቀጥሉት ሳምንታት እንደሚጀምር ገልጿል

ከሁለት ዓመት በፊት ወደ ኢትዮጵያ ገበያ የገባው ሳፋሪኮም ከትግራይ ክልል ውጪ በመላው አገሪቱ የቴሌኮም አገልግሎቱን ለደንበኞቹ ሲያቀርብ ቆይቷል፡፡

በትግራይ ክልል በነበረው ጦርነት ምክንያት የቴሌኮም አገልገሎቱን ማቅረብ ያልቻለው ይህ ኩባንያ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ አገልግሎት እጀምራለሁ ብሏል፡፡

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዊም ቫንሔለፑት ወደ ትግራይ ክልል አምርተው ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳድር አመራሮች ጋር መምከራቸውን ድርጅቱ በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል፡፡

በሚቀጥሉት ሳምንታት በትግራይ ክልል የኔትወርክ እና የመሠረተ ልማት ዝርጋታ ለማካሄድ በሚያስችለውን ውይይት ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር አድርጓል፡፡

ዋና ሥራ አስፈጻሚው እና ሌሎች ሰራተኞች ወደ መቀሌ ከተማ ተጉዘው ከጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ እና በክልል ካቢኔ የመሠረት ልማት ጉዳዮች ኃላፊ የዓለም ፀጋይ ጋር ተወያይቷል፡፡

ከ25 በላይ የኢትዮጵያ ከተሞች የቴሌሎም አገልግሎቱን እየሰጠ ያለው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የደንበኞቹ ቁጥር ከአንድ ሚሊዮን በላይ እንደደረሱለትም አስታውቋል።

ድርጅቱን ላለፉት ሁለት ዓመታት በስራ አስፈጻሚነት ሲመሩ የቆዩት አንዋር ሶሳ ባሳለፍነው ሀምሌ ወር ላይ ከሀላፊነት መነሳታቸው ይታወሳል።

በአንዋር ሶሳ ምትክም ቤልጂየማዊው የቀድሞ ኤምቲኤን ኡጋንዳ ሀላፊ የነበሩት ዊም ቫንሄልፑት ከመስከረም ጀምሮ ድርጅቱን በመምራት ላይ ይገኛሉ።

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሞባይል ፋይናንስ አገልግሎት የሆነው ኤምፔሳ (M-PESA) ባሳለፍነው ነሀሴ ጀምሮ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የአገልግሎት ፍቃድ አግኝቶ ዝራ መጀመሩ ይታወሳል፡፡

በኢትዮጵያ ያለው የጸጥታ ሁኔታ፣ የዋጋ ንረት እና በተወሰኑ ክልሎች የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ በሳፋሪኮም ትርፋማነት ላይ ጉዳት ጉዳት አድርሷል ብሏል፡፡

በሁለት ዓመት ውስጥ ከአምስት ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን ያፈራው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በቀጣዮቹ 10 ዓመታት ውስጥ 98 በመቶ ኢትዮጵየዊያንን ደንበኞቹ የማድረግ እቅድ እንዳለውም አስታውቋል፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *