ጋዜጠኛ የኋላሸት ዘሪሁን መታሰሩ ተገለጸ

የትርታ ኤፍ  ኤም መስራች ጋዜጠኛ የኋላሸት ዘሪሁን በፌደራል ፖሊሶች ተይዞ መወሰዱን ባለቤቱ ገልፃለች።

ጋዜጠኛ የኋላሸት ዘሪሁን ዛሬ ምሳ ሰዓት ላይ ባልዳራስ ኮንዶሚኒየም ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ በፌደራል ፖሊስ አባላት ተይዞ  ሜክሲኮ የቀድሞው የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ወደሚገኘው ጊዜያዊ ማቆያ ቦታ መወሰዱን ባለቤቷ ገልፃለች ።

ባለቤቱ የታሰረበት ቦታ ሄዳ የጠየቀች ሲሆን በምን ምክንያት እንደታሰረ እንዳላወቀና ለጥያቄም እንዳልቀረበ አሳውቋታል ።

ጋዜጠኛ የኋላሸት ትኩረቱን በኪነ ጥበባዊ ጉዳዮች ላይ ያደረገው ኪነ ብስራት የተሰኘ የሬድዮ ሾው ለዓመታት በብስራት ኤፍ ኤም 101.1 በማቅረብ ይታወቃል።

ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች ጥበቃ ቡድን ወይም ሲፒጂ ከቀናት በፊት ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ የጋዜጠኞች እስር መቀጠሉን እና የታሰሩት እንዲፈቱ ማሳሰቡ ይታወሳል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *