ፓስተር ዮናታን የ77 ሚሊዮን ብር የባንክ እዳ እንዳለባቸው ተገለጸ

በፓስተር ዮናታን ንብረቶች ላይ ንብ ባንክ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ አወጣ።

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ ላበደረው ንብረት የሐራጅ ሽያጭ አውጥቷል።

ንብ ባንክ በሰኔ 22 ቀን የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ባስወጣው የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ መሰረት በአዲስ አበባ እና ሀዋሳ ባሉ የመኖሪያ ቤት እና ንግድ ድርጅቶችን ለመሸጥ ለተጫራጮች ማስታወቂያ አውጥቷል።

አበዳሪው ወይም የመያዢያ ሰጪ ስም፣ አበዳሪው ቅርንጫፍ፣ የሚሸጠው ንብረት ዓይነትና የሚገኝበት ቦታ፣ የሐራጁ መነሻ በብር፣ የሐራጁ ቀንና ሰዓትም ተገልጿል።

ጨረታ ከወጣባቸው ንብረቶች መካለም አቶ ዮናታን አኪሊሉ አንጀሎ አራት ኪሎ ፕሪሚየም፣ በስማቸው የተመዘገበ ሀዋሳ ምሥራቅ ከተማ የሚገኝ 400 ሜትር ካሬ ቦታ ያለው ባለ 3 ወለል መኖሪያ ቤት ሲሆን የሐራጁ መነሻ ዋጋ 22 ሚሊዮን ብር ተደርጓል።

ሌላኛው ጨረታ የወጣበት ንብረት በአቶ ዮናታን አክሊሉ አንጄሎ/ ዜብራ ሓላ/የተ/የግ/ማ / 4ኪሎ ፕሪምየም/ በዜብራ ግሪል ሓላ/የተ/የግ/ማ ስም የተመዘገበ ሀዋሳ ከተማ ምሥራቅ ክፍለ ከተማ የሚገኝ 1,271.83 ሜትር ካሬ ይዞታ ያለው ባለ 4/ባለ 2 እና ባለ 1 ወለል ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ህንፃዎችን በ30 ሚሊዮን ብር መነሻ ዋጋ ተጥሎባቸዋል።

በተጨማሪም አቶ ዮናታን አክሊሉ አንጄሎ ዜብራ ግሪል ሓላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር፣ አበዳሪው ቅርንጫፍ 4ኪሎ ፕሪምየም፣ በዜብራ ግሪል ሓላ/የተ/የግ/ማ ስም እየተመዘገበ።

እና አዲስ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ውስጥ የሚገኝ 500 ካሜ ይዞታ ያለው መኖሪያ ቤት፣ በ25 ሚሊዮን ብር መነሻ ለአንድ ወር የሚቆይ የሐራጁ ማስታወቂያ ወጥቶባቸዋል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *