ወይዘሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ ከሀላፊነት ለቀቁ
ከ2011 ዓ.ም ታህሳስ ወር ጀምሮ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ሆነው ስራ የጀመሩት ወይዘሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ በጠየና ምክንያት የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸውን ሰማያዊ ማረጋገጫ ባለው የፌስቡክ ገጻቸው ላይ ገልጸዋል፡፡
“ባለፉት አራት አመት ከስድስት ወራት ሶስት ህዝበ ውሳኔዎችን እና አገራዊ ምርጫን በማካሄድ እና ፓለቲካ ፓርቲዎችን በማስተዳደር የተሰጡኝን ሃላፊነቶች ህጋዊነት ፍትሀዊነት እና ቅንነትን በተከተለ ሁኔታ ለማከናወን ስጥር ቆይቻለሁ” ብለዋል።
“ሆኖም ጤናዬን በሚገባ ለመጠበቅ የረጅም ጊዜ እረፍት የሚያስፈልገኝ ሆኖ በመገኘቱ ከ ነሀሴ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቦርድ ሰብሳቢነቴ በገዛ ፍቃዴ መልቀቄን ለተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ጽህፈት ቤት ሰኔ 5 ቀን 2015 ዓ.ም አሳውቄያለሁ” ሲሉም አክለዋል።
ወይዘሪት ብርቱካን በምርጫ ቦርድ አብረዋቸው የሰሩ የተቋሙ ሰራተኞችን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችን እና ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እንዲሁም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን አመስግነዋል፡፡