ኢትዮ ቴሌኮም 52 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን ገለጸ

ድርጅቱ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ 103 ሚሊዮን ዶላር ማስገባቱንም አስታውቋል

ኢትዮ ቴሌኮም የበጀት ዓመቱን የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጸሙን ልሀዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቧል፡፡

የድርጅቱ ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ በሪፖርታቸው ላይ እንዳሉት ኢትዮ ቴሌኮም ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ 52 ቢሊዮን ብር ገቢ አግኝቷል፡፡

እንዲሁም ድርጅቱ በሰጣቸው አገልግሎቶች 103 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማስገባቱንም ስራ አስፈጻሚዋ ተናግረዋል፡፡

የመንግሥትና የንግድ ተቋማት የክፍያ ስርዓታቸውን በቴሌ ብር እንዲፈፅሙ በማድረግ 30.5 ሚሊየን በላይ የቴሌ ብር ተጠቃሚዎችን ማፍራት መቻሉም ተገልጿል፡፡

በአጠቃላይ በቴሌብር አማካኝነት ከ394 ቢሊየን ብር በላይ ግብይት መፈጸሙን ስራ አስፈጻሚዋ ተናግረዋል፡፡ 

በኢንተርኔት ላይ የተጣለው ገደብ ተቋሙን የሚመለከት ሳይሆን፤ በመንግሥት አካል የተጣለ ገደብ ስለሆነ ከሚመለከተው አካል በሚሰጥ ፍቃድ የሚነሳ መሆኑን ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ ከየካቲት ወር መጀመሪያ አንስቶ በኢንተርኔት አገልግሎቶች ማለትም በፌስቡክ፣ ሜሴንጀር፣ ቴሌግራም እና ቲክቶክ ላይ ገደብ መጣሉ ይታወሳል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም ባለፉት አምስት ዓመታት ከ31 ቢሊየን ብር በላይ የውጭ ምንዛሪ ኪሳራ እንደገጠመውም ተገልጿል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎቱን ከኢትዮጵያ ውጪ ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ለመቀጠል ጥናቶችን በማከናወን ላይ ሲሆን ከደቡብ ሱዳን መንግስት ጋር ባሳለፍነው ዓመት የሁለትዮሽ ስምምነት መፈራረሙ ይታወሳል፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *